አፌን ፡ በምሥጋና (Afen Be Misgana) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Lyrics.jpg


(4)

ጆሮዬን ፡ ልበሳ
(Joroyen Libsa)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

አፌ በዝማሬ አፌ በዝማሬ ተሞላ
አፌ በምስጋና አፌ በምስጋና ተሞላ

ወደኋላ ወደኋላ እያሰብኩ ወደኋላ
ይስመለጥከኝ ትዝ ብሎኝ ከነጣቂው ከተኩላ
ወደኋላ ወደኋላ እያሰብኩ ወደኋላ
የረዳኸኝ ትዝ ብሎኝ ጉልበቴ ሲላላ

በምስጋና በዝማሬ ወደ ደጅህ በደስታ እመጣለሁ
ብርቱ ንፋስ ሳያፈርሰኝ ባንተ ምህረት ዛሬን አይቻለሁ

እረዳት በሌለበት አገዘኝ ያንተ ምህረት
አይዞሽ ባይ በሌለንት ወደደኝ ያንተ ምህረት

አንተ እኮ ነህ ሞቴን የወሰድከው
አንተ እኮ ነህ ማቄን የቀደድከው
አንተ እኮ ነህ መንገዴን ያበራኸው
አንተ እኮ ነህ ስሜን የቀየርከው
አንተ እኮ ነህ የዘመኔ እርዝመት
አንተ እኮ ነህ የመንገዴ መብራት
አንተ እኮ ነህ ደስታን ያሳየኽኝ
አንተ እኮ ነህ ይሳቅን ያሳቀፍከኝ

በምስጋና በዝማሬ ወደ ደጅህ በደስታ እመጣለሁ
ብርቱ ንፋስ ሳያፈርሰኝ ባንተ ምህረት ዛሬን አይቻለሁ
እረዳት በሌለበት አገዘኝ ያንተ ምህረት
አይዞሽ ባይ በሌለንት ወደደኝ ያንተ ምህረት