ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (Tamagn New Egziabhier) - አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት
(Addis Ababa Amanuel Hebret)

Lyrics.jpg


(1)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት ፡ አልበሞች
(Albums by Addis Ababa Amanuel Hebret)

አፌን ፡ በሳቅ ፡ ሞላ ፡ ምላሴን ፡ በእልልታ
ጠላቴ ፡ ማቅ ፡ ለበሰ ፡ አከበረኝ ፡ ጌታ
አንገት ፡ አያስደፋ ፡ አምላኬ ፡ አያሳፍር
በፊቱ ፡ የሆንኩለት ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር

አዝ፦ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አምላኬ (፪x)

የኔን ፡ ላብ ፡ ለሌላ ፡ ከቶ ፡ አያሳልፍም
ውለታ ፡ ከፋይ ፡ ነው ፡ ወጨትን ፡ አይሰብርም
ሲደርስ ፡ በሰዓቱ ፡ ፈጥኖ ፡ ከተፍ ፡ ይላል
አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዳለው ፡ ያደርጋል

አዝ፦ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አምላኬ (፪x)

ፍርዱ ፡ አይዛባ ፡ ጻድቅ ፡ በመንገዱ ፡
ልጆቹን ፡ ያስባል ፡ ጌታ ፡ እንደፈቃዱ
ቢያጠፋ ፡ ቢያለማ ፡ ትክክለኛ ፡ ነው
አምላኬን ፡ ተሳሳትክ ፡ የሚለው ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው

አዝ፦ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አምላኬ (፪x)

በንጉሥ ፡ ቀለበት ፡ ማህተም ፡ ቢታተም
የአምላኬ ፡ ጉልበት ፡ ከመስራት ፡ አይዝልም
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ጌታ ፡ ይሽረዋል
ያከበሩትንም ፡ ጌታ ፡ ማክበር ፡ ያውቃል

አዝ፦ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አምላኬ (፪x)

አይቸኩል ፡ አይዘገይ ፡ አያልፍ ፡ ከስዓቱ
ሁሌ ፡ በመታመን ፡ እንሁን ፡ በፊቱ
ቀንዳችንን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በጊዜው ፡ ያደርጋል
ሐናን ፡ እንዳሰበ ፡ እኛንም ፡ ያስባል

አዝ፦ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አምላኬ (፪x)