ሰበብ ፡ ፈላልጌ (Sebeb Felalegie) - አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት
(Addis Ababa Amanuel Hebret)

Lyrics.jpg


(1)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት ፡ አልበሞች
(Albums by Addis Ababa Amanuel Hebret)

እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
ለእግዚአብሔር ፡ ለእግዚአብሔር
በብዙ ፡ ምስጋና ፡ ፊቱ ፡ እቆማለሁ (፬x)

ክበር ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ (፪x)

አይጠፋም ፡ ከህሊናዬ ፡ ያረክልኝ
በልቤ ፡ ጽላት ፡ ተጽፏል ፡ የዋልክልኝ
አይጠፋም ፡ ከህሊናዬ ፡ ያረክልኝ
በልቤ ፡ ክታብ ፡ ይኖራል ፡ የዋልክልኝ

ተጐትጉቼ ፡ አይደለም ፡ ጌታን ፡ የማመልከው
ስለተደረገልኝ ፡ ደግሞም ፡ ስለሚገባው ፡ ነው
ልቤን ፡ ፈነቃቅሎ ፡ ነድሎ ፡ የሚወጣ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምስጋና
የፍቅር ፡ እጅ ፡ መንሻ ፡ ቢሆንልኝ ፡ እስቲ ፡ ልሰዋለት ፡ ደስ ፡ እያለኝ

ክበር ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ (፪x)

አንድ ፡ ጊዜ ፡ ስለሁሌ ፡ ራስ ፡ ህን ፡ ሰጠኸኝ
የቀራንዮ ፡ ወዳጅ ፡ እኔን ፡ የወደድከኝ
ዛሬም ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ሆነህ ፡ የምትማልድልኝ
ከሞት ፡ ከሃጥያት ፡ እስራት ፡ ነፃ ፡ ያወጣኸኝ

ሰበብ ፡ ፈላልጌ ፡ ምክንያት ፡ ፈላልጌ ፡ ላሞጋግስህ (፪x)

አልጣጣም ፡ አለኝ ፡ ምስጋናዬ
ካረግክልኝ ፡ ጋራ ፡ በኑሮዬ (፪x)

የእለታት ፡ ዑደት ፡ በሚለዋውጡት ፡ እረፍት
አሳርፈኸኛል ፡ ለኔስ ፡ ሆኗል ፡ ሁሌ ፡ ሰንበት
ዓለም ፡ የማታውቀው ፡ የማትሰጠውን
ሰጥተኸኛል ፡ ሰላም ፡ አይምሮ ፡ የሚያልፈውን

ሰበብ ፡ ፈላልጌ ፡ ምክንያት ፡ ፈላልጌ ፡ ላሞጋግስህ (፪x)