ከአንተ ፡ ወዴት (Keante Wediet) - አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት
(Addis Ababa Amanuel Hebret)

Lyrics.jpg


(1)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት ፡ አልበሞች
(Albums by Addis Ababa Amanuel Hebret)

ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እንሄዳለን ፡ ጌታ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እንሄዳለን (፪x)

አንተኮ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ (፬x)
ካንተ ፡ ፍቅር ፡ አለብን (፫x)
ለዘላለም ፡ አንለይም ፡ አንተን

ታዲያ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ እንሆናለን
ኑሮ ፡ ካንተ ፡ ውጭ ፡ ምን ፡ ጣዕም ፡ ይገኛል
የሕይወታችን ፡ ጨው ፡ ቅመም ፡ አንተ ፡ ነህ
ሰው ፡ ያደረገን ፡ ለኛ ፡ ሰው ፡ ሆነህ (፭x)

በቃልህ ፡ ተመክረን ፡ ወግ ፡ ማዕረግ ፡ አይተናል
የምትለው ፡ ሁሉ ፡ እጅግ ፡ ተስማምቶናል
በፍቅርህ ፡ ነፍሳችን ፡ ዛሬም ፡ ተይዛለች
ያለ ፡ ኢየሱሴ ፡ አይሆንም ፡ ትላለች (፪x)

አንተ ፡ ታዋጣናለህ ፡ ጌታ ፡ ታዋጣናለህ
አንተ ፡ ታዛልቃለህ ፡ ኢየሱስ ፡ የዘላለም ፡ ነህ (፪x)

ከቤትህ ፡ ርቀን ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አንችልም
ከአንተ ፡ ተለይተን ፡ እርካታ ፡ አናገኝም
ከውሃ ፡ እንደወጣ ፡ ዓሣ ፡ እንሆናለን
ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ እንሻለን (፪x)

አንተ ፡ ታዋጣናለህ ፡ ጌታ ፡ ታዋጣናለህ
አንተ ፡ ታዛልቃለህ ፡ ኢየሱስ ፡ የዘላለም ፡ ነህ (፪x)