እኔስ ፡ በምህረትህ ፡ ብዛት (Enies Bemhereteh Bezat) - አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት
(Addis Ababa Amanuel Hebret)

Lyrics.jpg


(1)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት ፡ አልበሞች
(Albums by Addis Ababa Amanuel Hebret)

እኔስ ፡ በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ ገብቻለሁ
ከመድሃኒት ፡ ምንጮች ፡ በደስታ ፡ ውኃን ፡ እቀዳለሁ
ለዘላለም ፡ በቤትህ ፡ እኖራለሁ (፫x)

ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው
ጌታዬ ፡ ለኔ ፡ ያረከው
የለኝም ፡ ቃላት ፡ መግለጫ
ባወራው ፡ ከቁጥር ፡ በዛ
(፪x)

ሐጢዓቴን ፡ ነግረውህ ፡ እንድትፈርድብኝ
ከሳሾቼ ፡ አምጥተው ፡ ፊትህ ፡ ሲያቆሙኝ
ጥበብን ፡ ተናግረህ ፡ ነፃ ፡ አውጥተኸኛል
የነፍሴ ፡ መድሃኒት ፡ ሞገስ ፡ ሆነኸኛል

ውለታህ ፡ ከእምሮዬ ፡ በለጠብኝ ፡ ጌታዬ (፪x)
ስጦታህ ፡ ከእምሮዬ ፡ በለጠብኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

እንባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ አብሰሃል
ሃዘኔን ፡ በደስታ ፡ ለውጠሃል
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምስኪኑን ፡ አንስተህ ፡ አክብረሃል
(፪x)

ውለታህ ፡ ከእምሮዬ ፡ በለጠብኝ ፡ ጌታዬ (፪x)
ስጦታህ ፡ ከእምሮዬ ፡ በለጠብኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

በአንተ ፡ ያላገኘሁት ፡ ምን ፡ አለ
ፅዋዬ ፡ ሞላ ፡ ተትረፈረፈ
አላጐደልኩም ፡ ጌታዬ
ከፍ ፡ ያርግህ ፡ ሁሌ ፡ ምስጋናዬ
ከፍ ፡ ያርግህ ፡ ሁሌ ፡ ምስጋናዬ (፪x)

ውለታህ ፡ ከእምሮዬ ፡ በለጠብኝ ፡ ጌታዬ (፪x)
ስጦታህ ፡ ከእምሮዬ ፡ በለጠብኝ ፡ ጌታዬ (፪x)