እግዚአብሔር ፡ ወዶናል (Egziabhier Wedonal) - አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት
(Addis Ababa Amanuel Hebret)

Lyrics.jpg


(1)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት ፡ አልበሞች
(Albums by Addis Ababa Amanuel Hebret)

እግዚአብሔር ፡ ወዶናል
በጽድቁ ፡ ጠርቶናል (፪x)

አፍቅሮናል (፰x)

አብ ፡ ላንድያ ፡ ልጁ ፡ ፈፅሞ ፡ ሳይራራ
አሳልፎ ፡ ሰጠው ፡ ልጁን ፡ ለመከራ
የፍቅሩ ፡ ብዛት ፡ ስፋቱ ፡ ርዝመቱ
ተገልጦ ፡ አይተናል ፡ በኢየሱስ ፡ ምህረቱ (፰x)

ዘላለም ፡ ላይጠላን ፡ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ወዶናል
ከእጁ ፡ ሊያወጣን ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ይችላል
ፍቅሩ ፡ ለዘላለም ፡ ጽኑና ፡ ቋሚ ፡ ነው
ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ ዘመን ፡ የማይሽረው (፰x)

አስጨናቂያችንን ፡ ከእግራችን ፡ ሥር ፡ ጥሎ
አከበረን ፡ ጌታ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አስቀምጦ
በነፃነት ፡ ልንኖር ፡ አርነት ፡ ወጥተናል
ከሰይጣን ፡ ባርነት ፡ ቀንበር ፡ አምልጠናል (፰x)

እግዚአብሔር ፡ ወዶን ፡ ከሰማይ ፡ አሰበን
ከጥፋት ፡ ሊያድነን ፡ ልጁን ፡ ወደ ፡ እኛ ፡ ሰደደ (፪x)

በአሰራርህ ፡ ተደስተናል
አመራረጥህ ፡ እጅግ ፡ ገርሞናል
ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ አሃሃ
ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ ኦሆሆ (፪x)

ፍጥረት ፡ ያምልክህ ፡ አሃሃ
ፍጥረት ፡ ያምልክህ ፡ ኦሆሆ (፪x)