በነገርህ ፡ ፍጹም (Benegereh Fetsum) - አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት
(Addis Ababa Amanuel Hebret)

Lyrics.jpg


(1)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት ፡ አልበሞች
(Albums by Addis Ababa Amanuel Hebret)

በነገርህ ፡ ፍፁም ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር (፬x)

እንደሰው ፡ አይደለህ ፡ ሚዛንህ ፡ አባይ
በቅን ፡ ትፈርዳለህ ፡ ተቀምጠህ ፡ በላይ (፪x)

ሸንጋይ ፡ አንደበትም ፡ የለብህም
ሐጥኡን ፡ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትለውም (፪x)

ለሁሉ ፡ እንደሰራው ፡ ትከፍለዋለህ
በደል ፡ አትፈጽምም ፡ አድሎም ፡ የለብህም (፪x)

የሰው ፡ ይግባኝ ፡ ሰሚ ፡ ፍርድህ ፡ ትክክል ፡ ነው
አምላኬ ፡ እንዳንተ ፡ ቅን ፡ የሆነ ፡ ማነው

ማስተዋልህም ፡ አይመረመር
ሁሌ ፡ ጽድቅ ፡ ነው ፡ ፍርድህ ፡ እግዚአብሔር
ዓይንህ ፡ እንዳየ ፡ ጆሮህ ፡ እንደሰማ ፡ መች ፡ ትፈርዳለህ
ለአሕዛብ ፡ እንኳን ፡ በቅድስና ፡ ትበይናለህ