አንተ ፡ አትለወጥም (Ante Atelewetem) - አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት
(Addis Ababa Amanuel Hebret)

Lyrics.jpg


(1)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ አማኑኤል ፡ ህብረት ፡ አልበሞች
(Albums by Addis Ababa Amanuel Hebret)

ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ በነበረው ፡ ክብርህ
ዛሬም ፡ ሳትለወጥ ፡ አለህ ፡ በዙፋንህ
የዘላለም ፡ አምላክ ፡ የዘላለም ፡ ጌታ
አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መቼም ፡ አትረታ

አዝ፦ አንተ ፡ አትለወጥም ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ጌታ ፡ አትለወጥም ፡ ጌታ ፡ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ፡ ያው ፡ ነህ ፡ እንደትላንትናው ፡ ነህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ መቼ ፡ ትለወጣለህ (፪x)

በኛ ፡ ላይ ፡ አላማህ ፡ ዘላለም ፡ ፍቅር ፡ ነው
ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ ዘመን ፡ የማይሽረው
እግዚአብሔር ፡ ወደደን ፡ እስከመጨረሻው
ፍቅሩ ፡ አያሰጋ ፡ ወረትም ፡ አያውቀው (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ አትለወጥም ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ጌታ ፡ አትለወጥም ፡ ጌታ ፡ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ፡ ያው ፡ ነህ ፡ እንደትላንትናው ፡ ነህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ መቼ ፡ ትለወጣለህ (፪x)

ጥንት ፡ ከአባቶቻችን ፡ ጋር ፡ እንደነበርህ
እንደ ፡ ኃያል ፡ እንደ ፡ ጨካኝ ፡ አብረህ ፡ እንደወጣህ
ዛሬም ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ አብረህ ፡ ትወጣለህ
በሰልፉ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ ድል ፡ ትሰጠናለህ
(፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ አትለወጥም ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ጌታ ፡ አትለወጥም ፡ ጌታ ፡ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ፡ ያው ፡ ነህ ፡ እንደትላንትናው ፡ ነህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ መቼ ፡ ትለወጣለህ (፪x)

እስከ ፡ ዓለም ፡ ፍፃሜ ፡ ከእናንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ
እኔ ፡ አልለወጥም ፡ ዘመን ፡ አይሽረኝ
ብለህ ፡ እንደተናገርክ ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃልህ
እኛ ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ አንተም ፡ አልተለወጥክ (፭x)

አዝ፦ አንተ ፡ አትለወጥም ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ጌታ ፡ አትለወጥም ፡ ጌታ ፡ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ፡ ያው ፡ ነህ ፡ እንደትላንትናው ፡ ነህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ መቼ ፡ ትለወጣለህ (፪x)

መቼ ፡ ትለወጣለህ (፪x)
እንደትላንትናው ፡ ነህ (፪x)
መቼ ፡ ትለወጣለህ (፪x)
እንደትላንትናው ፡ ነህ (፪x)