ደራሽ (Derash) - አቤነዘር ፡ ታገሰ ፡ እና ፡ ኤደን ፡ እምሩ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አቤነዘር ፡ ታገሰ ፡ እና ፡ ኤደን ፡ እምሩ
(Abenezer Tagesse and Eden Emiru)

Lyrics.jpg


(Volume)

ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Singles)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአቤነዘር ፡ ታገሰ ፡ እና ፡ ኤደን ፡ እምሩ ፡ አልበሞች
(Albums by Abenezer Tagesse and Eden Emiru)

ደራሽ ፡ አለ ፡ ካህናችሁ
ከኢየሱስ ፡ ውጪ ፡ ማን ፡ አለ
ጠበቃ ፡ አለ ፡ ካህናችሁ
ከአባቴ ፡ ውጪ ፡ ማን ፡ አለ

አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ ፡ በእኔና ፡ በሞት
ጣልቃ ፡ ገብቶ ፡ አዳነኝ ፡ ድንገት ፡ በድንገት(፪)

አልተወኝም ፡ እንዲሁ ፡ እንዲሁ ፡ እንደዘበት
በድንገት ፡ ደረሰ ፡ ስሽቀዳደም ፡ ለሞት
አበቃለት ፡ ያለው ፡ የታለ ፡ ጠላቴ
ሞቴን ፡ ሲጠባበቅ ፡ ክብር ፡ ገባ ፡ ቤቴ

ለካ ፡ የመጨረሻውን ፡ አውቆ
የጠላቴ ፡ ድንፋታው ፡ አልቆ
በእጁ ፡ ድንገት ፡ ያስገባኝ ፡ ሲመስለው
ጌታ ፡ መጥቶ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየረው

ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለክብሩ ፡ ዘላለም
እውነተኛ ፡ ዳኛ ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የለም
የነፍሴ ፡ መዳኛ ፡ የክፉ ፡ ቀን ፡ ደራሼ
ስሙን ፡ ላወድሰው ፡ መልሼ ፡ መልሼ

"ትግርኛ" (ኤደን ፡ እምሩ)

?? ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ እንደርሱ
ፈጥኖ ፡ ሚያወጣ ፡ በድንገት ፡ ደርሶ
አዳኝ ፡ ደራሽ ፡ ማነው ፡ ካህናችሁ
በምሥጋናዬ ፡ ኑ ፡ ልንገራችሁ

እንኳን ፡ አበቃ ፡ ሲባል ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ደርሶ ፡ ከሞት ፡ የሚያድን ፡ ውድዬ ፡ ነው
ባማረ ፡ ዜማ ፡ ክብርን ፡ ልሰዋለት
ብዙ ፡ ውዳሴ ፡ ዕልልታ ፡ ይሁንለት

"ትግርኛ" (አቤኔዘር ፡ ታገሰ)