አባል:Tarekegn Hadaro

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የገነባውን ፡ አፈራረሰ

  የጠለለውን ፡ አደፈረሰ
  የተከለውን ፡ ነቅሎ ፡ ጣለና
  የእግዚአብሔርን ፡ ቤት ፡ አስቀረው ፡ ኦና::

ያንን ፡ ሰው ፡ 4 ጌታ ፡ መልሰው

ድንግሉን ፡ መሬት ፡ አርሶ ፡ ጎልጉሎ በብዙ ፡ ድካም ፡ ዘሩን ፡ በትኖ ግን ፡ አልታገሰም ፡ ሮጦ ፡ ፈርጥጡዋል የተዘራው ፡ ዘር ፡ በአረም ፡ ተውጥዋል::

ያንን ፡ ሰው ፡ 4 ጌታ ፡ መልሰው::

በዓለም ፡ ተንቆ ፡ ሞኝ ፡ ተብሎ ፡ ስድብ ፡ ግልምጫውን ፡ ነቀፋ ፡ ችሎ ፡ አክሊል ፡ ሊሰጠው ፡ ጌታ ፡ ሲመጣ ፡ ኮብልሎ ፡ ኖሮ ፡ ከቦታው ፡ ታጣ ::

ያንን ፡ ሰው ፡ 4 ጌታ ፡ መልሰው

ህዝብን ፡ ሊጠብቅ ፡ መንጋን ፡ ሊመራ ፡ በመከር ፡ ጊዜ ፡ ዘር ፡ እንድዘራ ፡ መክሊት ፡ ሰጥተሄው ፡ አልነበረም ፡ ወይ ታዲያ ፡ ያንን ፡ ሰው ፡ አትመልሥም ፡ ወይ::