የዳዊት ፡ መሻት (Yedawit Meshat) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

ዓለምን ፡ ሁሉ ፡ አትርፌ ፡ ነፍሴን ፡ ግን ፡ በከንቱ ፡ ባጐድል
ለጊዜያዊ ፡ ነገር ፡ ብዬ ፡ እራሴን ፡ ስገኝ ፡ ስደልል
አልፈልግም ፡ እራሴን ፡ ማየት ፡ ለከንቱ ፡ ነገር ፡ ስንከራተት
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ምለምንህ ፡ እንድኖር ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ በፊትህ (፪x)
በፊትህ ፡ እንድኖር ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ በፊትህ

ከዓለም ፡ እልፍ ፡ ቀን ፡ ይልቅ ፡ ከመኖር ፡ ከህልውና ፡ እሮሮ
አንድ ፡ ቀን ፡ ቤትህ ፡ ይሻላል ፡ መሸምገል ፡ ደግሞ ፡ እጅግ ፡ ይበልጣል
ግን ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ እለምንሃለሁ ፡ እሷንም ፡ ደግሞ ፡ እጅግ ፡ እሻለሁ
በቤትህ ፡ ውስጥ ፡ ቀሪ ፡ ዘመኔን ፡ እያየሁ ፡ መኖር ፡ ነው ፡ ውበትህን
ውበትህን ፡ እያየሁ ፡ መኖር ፡ ነው ፡ ውበትህን ፡ ኦሆሆሆ
ውበትህን ፡ እያየሁ ፡ መኖር ፡ ነው ፡ ውበትህን

በውበት ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ሆሆሆ ፡ ስትስቅ ፡ ከሰማይ
አምልኮ ፡ ያስጨምረኛል ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምን ፡ ያረካኛል
ከወደደከው ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ እይዘመርኩ ፡ መኖር ፡ ብቻ ፡ ነው
ደስ ፡ ካለህ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ እየዘመርኩ ፡ መኖር ፡ ብቻ ፡ ነው

መሻቴ ፡ ጉጉቴ ፡ ይሄ ፡ ነው
አንተ ፡ ደስ ፡ ካለህ ፡ ደስ ፡ ካለህ
ምን ፡ እፈልጋለሁ ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ አመልክሃለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ እያመለኩ ፡ መኖር ፡ ብቻ ፡ ነው
ደስ ፡ ካለህ ፡ ምን ፡ እላለሁ
እየዘመርኩ ፡ መኖር ፡ ብቻ ፡ ነው