የኢየሱስ ፡ ደም (YeEyesus Dem) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

የኃጢአቴ ፡ መብዛት ፡ ጐልቶ ፡ ይታየኛል
እርሱን ፡ መበደሌ ፡ በደምብ ፡ ታውቆኛል
ይህንን ፡ በሙሉ ፡ ሳስበው ፡ ብፈራም
ኃጢአቴ ፡ የበረታ ፡ መስሎ ፡ ቢሰማኝም

አዝ፦ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ለእኔ ፡ የፈሰሰው
አንዳች ፡ ሳያስቀር ፡ በደሌን ፡ አጠበው
የኃጢአት ፡ ፍርሃት ፡ ከእኔ ፡ ተወግዷል
በደሙ ፡ ያለው ፡ ኃይል ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል

ኃጢአተኛ ፡ እንደሆንኩ ፡ እግዚአብሔርም ፡ ያውቃል
ለዚህም ፡ እንዲሆን ፡ ልጁን ፡ ልኮልኛል
ከኃቲአቴ ፡ እና ፡ ከበደሌ ፡ ኃይል
የክርስቶስ ፡ ደም ፡ ጉልበት ፡ እጅግ ፡ ይበረታል

አዝ፦ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ለእኔ ፡ የፈሰሰው
አንዳች ፡ ሳያስቀር ፡ በደሌን ፡ አጠበው
የኃጢአት ፡ ፍርሃት ፡ ከእኔ ፡ ተወግዷል
በደሙ ፡ ያለው ፡ ኃይል ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል

ነጻ ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል ፡ ኦሆሆ

እኔን ፡ ሲታደገኝ ፡ ከዘለዓለም ፡ ሞት
ጐሳና ፡ ቀለሜን ፡ እርሱን ፡ መቼ ፡ አግቶት
ዘሬና ፡ ቋንቋዬ ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ ምንም
ደሙ ፡ እኔን ፡ ለማዳን ፡ ፈጽሞ ፡ አልደከመም

አዝ፦ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ለእኔ ፡ የፈሰሰው
አንዳች ፡ ሳያስቀር ፡ በደሌን ፡ አጠበው
የኃጢአት ፡ ፍርሃት ፡ ከእኔ ፡ ተወግዷል
በደሙ ፡ ያለው ፡ ኃይል ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል

የኢየሱስ ፡ ደሙ ፡ ብርቱ ፡ ነው
ኃይል ፡ አለው ፡ ጉልበት ፡ አለው
ኃጢአቴን ፡ አጠበው (፫x)

አጠበው