ያልከው ፡ ይሆናል (Yalkew Yehonal) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

ፈቃድህ ፡ ሆኖ ፡ ነው ፡ ትላንትን ፡ የኖርኩት
ፈተናን ፡ መጽናት ፡ ለማለፍ ፡ የቻልኩት
በራሴማ ፡ ቢሆን ፡ በገዛ ፡ ፍቃዴ
ትላንትን ፡ አልውልም ፡ እንኳን ፡ ልኖር ፡ ዛሬን

አዝ፦ ምሥጋና ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሆናል
እኔ ፡ ሰው ፡ ስለሆንኩ ፡ አይመስለኝም
ይሆናል ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ምች ፡ ይቀራል

ሃሳብህ ፡ ሆኖ ፡ ነው ፡ አሁን ፡ የምኖረው
የማልፍበት ፡ መንገድ ፡ አንተ ፡ ያየኸው ፡ ነው
ስለእኔ ፡ ማታውቀው ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ የለም
ማስበው ፡ ማደርገው ፡ ከአንተ ፡ አልተሰወረም

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሆናል
እኔ ፡ ሰው ፡ ስለሆንኩ ፡ አይመስለኝም
ይሆናል ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ምች ፡ ይቀራል

ወደ ፡ ፊት ፡ ምኖረው ፡ ያልደረስኩበትን
ያልኖርኩበትን ፡ ቀን ፡ ገና ፡ ያላየሁትን
ተስፋ ፡ አለኝ ፡ እንድኖር ፡ ከአፍህ ፡ በወጣው ፡ ቃል
እኔ ፡ ያልኩት ፡ ሳይሆን ፡ ያልከው ፡ ይፈጸማል

እኔስ ፡ እንደራሴ/ስለራሴ ፡ ከማስበው ፡ ይልቅ
አንተ ፡ የተናገርከው ፡ የመሰከርክልኝ ፡ ትንቢት
ስለዚህ ፡ በደስታ ፡ ራሴን ፡ ሰጥሃለሁ
ትካዜዬን ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ጥላለሁ (፪x)