ተናገር (Tenager) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

እስከዛሬ ፡ ፊትህ ፡ ቀርቤ ፡ የልቤን ፡ ነግሬሃለሁ
እንዲሆንልኝ ፡ አስቤ ፡ ጠይቄሃለሁ
ፍላጐቴን ፡ በሙሉ ፡ አሰምቼሃለሁ
እስክትፈጽምልኝ ፡ ጐትጉቼሃለሁ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በፊትህ ፡ ያለሁት ፡ ልናገር ፡ አይደለም
ምን ፡ እንደምትል ፡ ሃሳብህን ፡ ለማወቅ
ልሰማ ፡ መጥቻለሁኝ ፡ ተናገር

ዛሬስ ፡ የአንተ ፡ ጊዜ ፡ እንዲሆን ፡ አንተ ፡ እንድትናገር
ፈቃድህ ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ እንድትገልጽልኝ
ምን ፡ እንዳደርግልህ ፡ እንደምትፈልግ
ስትናገር ፡ ልሰማ ፡ መጥቻለሁኝ
ንገረኝ ፡ ምን ፡ እንዳደርግልህ ፡ ትወዳለህ
እንዴ ፡ እንድኖር ፡ ትፈልጋለህ
ልሰማ ፡ መጥቻለሁኝ ፡ ተናገር
ተናገር (፫x) ፡ ልሰማ ፡ አለሁ ፡ ተናገር
ተናገር (፪x) ፡ እሰማሃለሁ ፡ ተናገር

ተናገር (፪x)
እሰማሃለሁ ፡ ተናገር