ምንያህል ፡ በአንተ (Menyahel Bante) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 3:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

ደግ ፡ ሰው ፡ መሆኔ ፡ የተነገረልኝ
በመልካም ፡ መግባሬ ፡ የተመሰገንኩኝ
እንዳልሆንኩ ፡ እያወቁ ፡ ወዳንተ ፡ አስጠጋኸኝ
ማንንነትህ ፡ ፍቅር ፡ ስለሆነ ፡ ወደደከኝ

አዝ፦ ምን ፡ ያህል ፡ በአንተ ፡ የተወደደኩ ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምን ፡ ያህል ፡ በአንተ ፡ የተወደደኩ ፡ ነኝ
ፍቅርህ ፡ ማርኮኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ያደረገኝ

ዐይኖችህ ፡ ዘወትር ፡ ይመለከቱኛል
ጆሮዎችህ ፡ የልቤን ፡ ጪኸት ፡ ያደምጡኛል
በኑሮ ፡ ውጣ ፡ ውረድ ፡ መጓዝ ፡ ቢያቅተኝም
ተሸከምከኝ ፡ እንጂ ፡ ፈጽሞ ፡ አልተውከኝም

አዝ፦ ምን ፡ ያህል ፡ በአንተ ፡ የተወደደኩ ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምን ፡ ያህል ፡ በአንተ ፡ የተወደደኩ ፡ ነኝ
ፍቅርህ ፡ ማርኮኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ያደረገኝ

በድካሜ ፡ አግዘኸኝ ፡ ጥፋቴን ፡ ሳትቆጥርብኝ
ከቁጣ ፡ ቀደመ ፡ ፍቅርህ ፡ ትወደኛለህ ፡ ደግ ፡ አባት ፡ ነህ (፫x)