ሌት ፡ ይነጋል (Liet Yenegal) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

ዕውቀት ፡ ስለአንተ ፡ ቢበዛ ፡ ደግ ፡ ነው
እምነት ፡ ያለስራ ፡ ግን ፡ ከንቱ ፡ ነው
እምነቴ ፡ ሲፈተን ፡ በመከራው ፡ ብዛት
ስጨነቅ ፡ በራሴ ፡ ሲውጠኝ ፡ ፍርሃት

ለመቼ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ማለቴ
አብሮኝ ፡ አለ ፡ ያልኩት ፡ ረዳቴ
ያገባሃል ፡ በእኔ ፡ ሕይወት ፡ እያልኩኝ
በራሴ ፡ ነገሬን ፡ ከጨረስኩኝ

በመልካም ፡ ቀን ፡ አምንሃለሁ ፡ ስልህ
በክፉ ፡ ቀን ፡ አለህ ፡ ሆይ ፡ ሳልልህ
እኔ ፡ እንዳልቀረሁ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ ፡ ጌታ
ቃሌ ፡ አምናለሁ ፡ በስራህ ፡ . (1) .

አምንሃለሁ ፡ ቃሌ ፡ አይበጀኝም
የቃሌ ፡ ብዛት ፡ እኔን ፡ አልሰራኝም???. (2) .
ተግባሩ ፡ እንጂ ፡ ቢበዛም ፡ ሳንኮፉ???. (3) .
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሁሉን ፡ እያለፉ

ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያርፋል
ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያድራል (፪x)
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያድራል
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ያርፋል ፡ የታመነ

የሠማይ ፡ ወፎች ፡ አይዘሩም ፡ አያጭዱም
ለነገም ፡ አስበው ፡ ከጐተራም ፡ አይከቱም
እነሱን ፡ ያተገብክ ፡ አንተ ፡ ደግ ፡ አባት ፡ ነህ
እኔማ ፡ ልጅህ ፡ ነኝ ፡ ምልህ ፡ ትሆናለህ

ለመቼ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ማለቴ
አብሮኝ ፡ አለ ፡ ያልኩት ፡ ረዳቴ
ያገባሃል ፡ በእኔ ፡ ሕይወት ፡ እያልኩኝ
በራሴ ፡ ነገሬን ፡ ከጨረስኩኝ

ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያርፋል
ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያልፋል
ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያድራል (፪x)