From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አንድ ፡ ቀን ፡ ይመጣል ፡ ልብ ፡ ማይዝልበት
ደመናና ፡ ጭጋግ ፡ እምባም ፡ የሌለበት
በወርቃማው ፡ ምድር ፡ ሁሉም ፡ ሰላም ፡ ሆኖ
ምን ፡ ዓይነት ፡ ክቡር ፡ ቀን ፡ ይሆናል
አዝ፦ ምን ፡ ዓይነት ፡ የከበረ ፡ ቀን ፡ ይሆን ፡ ጌታን ፡ ሳይ
ፊቱን ፡ ስመለከት ፡ በፀጋው ፡ ያዳነኝን
በእጁም ፡ ይዞኝ ፡ ሲሄድ ፡ ወደ ፡ ተስፋው ፡ ሃገር
ምን ፡ ዓይነት ፡ ክቡር ፡ ቀን ፡ ይሆናል
ሞት ፡ የለም ፡ በዚያ ፡ ድካም ፡ መንገላታት
ረሃብና ፡ መጠማት ፡ የለም ፡ የራስ ፡ ምታት
ፈዋሹ ፡ መድህን ፡ ይኖራል ፡ ከእኛ ፡ ጋር
ምን ፡ ዓይነት ፡ ክቡር ፡ ቀን ፡ ይሆናል
አዝ፦ ምን ፡ ዓይነት ፡ የከበረ ፡ ቀን ፡ ይሆን ፡ ጌታን ፡ ሳይ
ፊቱን ፡ ስመለከት ፡ በፀጋው ፡ ያዳነኝን
በእጁ ፡ ይዞኝ ፡ ሲሄድ ፡ ወደ ፡ ተስፋው ፡ ሃገር
ምን ፡ ዓይነት (ምን ፡ ዓይነት)፡ ክቡር ፡ ቀን (ክቡር ፡ ቀን)፡ ይሆናል
ሃዘን ፡ የለም ፡ ጭንቀት ፡ ለቅሶ ፡ የለ ፡ ጩኸት
ህመም ፡ የለም ፡ ስሜት ፡ ንፍገጥ ፡ አይሆን ፡ መጥላት
ከሞተልን ፡ ጋራ ፡ ለዘለዓለም ፡ መኖር
ምን ፡ ዓይነት ፡ ክቡር ፡ ቀን ፡ ይሆናል
አዝ፦ ምን ፡ ዓይነት ፡ የከበረ ፡ ቀን ፡ ይሆን ፡ ጌታን ፡ ሳይ
ፊቱን ፡ ስመለከት ፡ በፀጋው ፡ ያዳነኝን
በእጁ ፡ ይዞኝ ፡ ሲሄድ ፡ ወደ ፡ ተስፋው ፡ ሃገር
ምን ፡ ዓይነት (ምን ፡ ዓይነት) ፡ ክቡር ፡ ቀን ፡ ይሆናል
ምን ፡ ዓይነት ፡ ክቡር ፡ ቀን ፡ ይሆናል (፪x)
|