ፍቅርህ ፡ ነው (Feqereh New) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

የመዳኔ ፡ ምክንያት ፡ ምህረት ፡ የማግኘቴ
አንተ ፡ ነህ ፡ እንጂ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ከእኔ
ይህ ፡ ስለገባኝ ፡ አመሰግናለሁ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ለአንተ ፡ እዘምራለሁ

ነፍስህን ፡ እስከመስጠት ፡ ድረስ ፡ ወደኸኛል ፡ ጌታዬ
ለእኔ ፡ ለኀጢአተኛው ፡ በመስቀል ፡ ሞተሃል ፡ ጌታዬ (፪x)

አዝ፦ አምላኬ ፡ ሄሄ ፡ ኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ ለአንተ ፡ እዘምርልሃለሁ
ኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ ለአንተ ፡ እዘምርልሃለሁ

አይደለም ፡ እንደኔ ፡ እንደኀጢአቴ ፡ ብዛት
አምላክ ፡ ያሳየኸኝ ፡ የምህረትህን ፡ ስፋት
እንዲሁ ፡ በጸጋህ ፡ ፍቅርህ ፡ አድኖኛል
ለመውደድህ ፡ ምላሽ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል

እግሮቼን ፡ ከጥፋት ፡ መልሰሃልና ፡ ጌታዬ
ሳጸለች ፡ በፍቅር ፡ ይዘኸኛልና ፡ ጌታዬ
እግዚአብሔር ፡ ከጥፋት ፡ መልሰሃልና ፡ ጌታዬ
ሳጸለች ፡ በፍቅር ፡ ይዘኸኛልና ፡ ጌታዬ

አዝ፦ አምላኬ ፡ ሄሄ ፡ ኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ ለአንተ ፡ እዘምርልሃለሁ
ኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ አመሰግናለሁ
ኦኦኦኦ ፡ ሁልጊዜ ፡ ለአንተ ፡ እዘምርልሃለሁ

አዝፍቅርህ ፡ ነው (፬x)
የማረኝ ፡ ያዳነኝ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ ነው
አዲስ ፡ ሰው ፡ ያረገኝ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ ነው
የማረኝ ፡ ያዳነኝ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ ነው
ሕይወትን ፡ የሰጠኝ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ ነው (፪x)

ፍቅርህ ፡ ነው (፬x)