ዕውቀትህ ፡ ትልቅ ፡ ነው (Ewqeteh Teleq New) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

ሁልጊዜ ፡ ሳስበው ፡ ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ነገር
የእኔ ፡ ሁለንተና ፡ ከአንተ ፡ አልመሰወር
መንገዴን ፡ ሃሳቤን ፡ ፍለጋዬን ፡ ሁሉ
መርምረህ ፡ አወቅህ ፡ ሕይወቴን ፡ በሙሉ (፪x)

ሰዎች ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሚያውቁት ፡ የተወሰነ ፡ ነው
የሚናገሩት ፡ ሁሉ ፡ ሚያዩትን ፡ ብቻ ፡ ነው
. (1) . ፡ ከአንተ ፡ ጨለማ ፡ ይሰውረኛል ፡ ብል
ሌሊት ፡ በዙሪያዬ ፡ ብርሃን ፡ ይሆናል (፪x)

ከመንፈስህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ከፊትህስ ፡ ርቄ ፡ የት ፡ እሸሻለሁ (፪x)

በሁሉ ፡ ቦታ ፡ ትኖራለህ
ዕውቀትህ ፡ ለእኔ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነው
ልደርስበት ፡ የማልችል ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው (፬x)

ከመንፈስህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ከፊትህስ ፡ ርቄ ፡ የት ፡ እሸሻለሁ