አንተን ፡ እባርክሃለሁ (Anten Ebarkehalehu) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

አሁን ፡ ከገጠመኝ ፡ ፈተና ፡ በስተጀርባ
ድል ፡ እንዳለ ፡ አውቃለሁ ፡ ሚሆን ፡ ከአንተ ፡ ጌታ
ስለዚህ ፡ ይህንን ፡ መከራ ፡ ሳስበው
ከኋላ ፡ ያለውን ፡ ድል ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ

አዝ፦ ከልቤ ፡ አንተን ፡ እባርክሃለሁ
ወድጄ ፡ ለአንተ ፡ እገዛልሃለሁ (፪x)

የማማርርበት ፡ ምክንያት ፡ አንድ ፡ የለኝም
ለገጠመኝ ፡ ችግር ፡ አላጉረመርምም
ለምን ፡ ቢባል ፡ ሁሉም ፡ በጐ ፡ ታደርጋለህ
ለመልካም ፡ ለውጠህ ፡ ታስደንቀኛለህ

አዝ፦ ከልቤ ፡ አንተን ፡ እባርክሃለሁ
ወድጄ ፡ ለአንተ ፡ እገዛልሃለሁ (፪x)

ስለምትሰማኝ ፡ እነግርሃለሁ (እነግርሃለሁ)
ስለምትረዳኝ ፡ እታመንሃለሁ (እታመንሃለሁ)
ስለምትይዘኝ (ስለምትይዘኝ) ፡ እደገፍሃለሁ
ሆሆሆሆ ፡ ሆሆሆ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)