አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነው (Amlakie Feqer New) - ዜማ ፡ ለክርስቶስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዜማ ፡ ለክርስቶስ
(Zema 4 Christ)

Zema 4 Christ 2.jpg


(2)

ክቡር ፡ ቀን
(Kebur Qen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 3:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዜማ ፡ ለክርስቶስ ፡ አልበሞች
(Albums by Zema 4 Christ)

ለክብሩ ፡ ሳይገደው ፡ ከሠማይ ፡ ወረደ
እኔኑን ፡ ለማዳን ፡ ራሱን ፡ ዝቅ ፡ አደረገ
እንዲህ ፡ እንዲወደኝ ፡ ነፍሱን ፡ እንዲሰጠኝ
ከእኔ ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልተገኘም

ለሰላሙ. (1) . ፡ ሃጥያት ፡ የተፈረደብኝ
የዘለዓለም ፡ ሞት ፡ ነበር ፡ የሚገባኝ
አላስችል ፡ ስላለው ፡ ለእኔ ፡ ያለው ፡ ፍቅር
መሰቀል ፡ መረጠ ፡ ከአባቱ ፡ ክብር

አስደናቂ ፡ ፍቅሩን ፡ ለእኔ ፡ የገለጠው
አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነው (፬x)
 
የእኔን ፡ ሞት ፡ ሞቶ ፡ ሕይወትን ፡ ሰጥቶኛል
እርሱ ፡ ተሰቃይቶ ፡ በፍቅር ፡ ወልዶኛል
ደህንነት ፡ አግኝቼ ፡ በደስታ ፡ ምኖረው
ያቆመኝ ፡ በሕይወት ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነው

አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነው
አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነው
አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነው
ኦሆሆ ፡ ፍቅር ፡ ነው (፭x)