From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
"አልተወውም ፡ አለቀውም ፡ መድሃኒቴን
የሰላሜን ፡ ጌታ ፡ እረፍት ፡ የሰጠኝን
ጌታ ፡ ኢየሱስን ፡ ኦሆሆ"
አዝ፦ አልተወውም ፡ አለቀውም ፡ መድሃኒቴን
የሰላሜን ፡ ጌታ ፡ እረፍት ፡ የሰጠኝን
ጌታ ፡ ኢየሱስን (፪x)
መግቢያ ፡ መውጫ ፡ አጥቼ ፡ ስንከራተት ፡ በዓለም
አጽናናኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነይ ፡ የእኔ ፡ ነሽ ፡ አለኝ
ጥሪውንም ፡ ሰማሁ ፡ ሕይወቴም ፡ ረካሁ
መቅበዝበዜም ፡ ቀረ ፡ ነፍሴም ፡ ተደሰተች
አዝ፦ አልተወውም ፡ አለቀውም ፡ መድሃኒቴን
የሰላሜን ፡ ጌታ ፡ እረፍት ፡ የሰጠኝን
ጌታ ፡ ኢየሱስን
ኃያሉ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው
ማቄን ፡ የቀደደ ፡ እንባዬን ፡ ያበሰው
ሰላም ፡ ኧረፍት ፡ ሰጥቶኝ ፡ መድሃኒት ፡ የሆነኝ
ተስፋዬን ፡ አድሶ ፡ በቃሉ ፡ ያጸናኝ
አዝ፦ አልተወውም ፡ አለቀውም ፡ መድሃኒቴን
የሰላሜን ፡ ጌታ ፡ እረፍት ፡ የሰጠኝን
ጌታ ፡ ኢየሱስን ፡ ኦሆሆ
ለነፍሴ ፡ እረፍት ፡ ሆነ ፡ ቀለለ ፡ ሸክሜ
መጨነቄ ፡ ቀረ ፡ ፈሰሰ ፡ ሰላሜ
ፀጋን ፡ አለበሰኝ ፡ ነውሬንም ፡ ሸፈነ
ልገዛለት ፡ እንጂ ፡ እርሱን ፡ እንዴት ፡ ልተው (፪x)
አዝ፦ አልተወውም ፡ አለቀውም ፡ መድሃኒቴን
የሰላሜን ፡ ጌታ ፡ እረፍት ፡ የሰጠኝን
ጌታ ፡ ኢየሱስን
|