From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ነፍሴን ፡ ማርከህ ፡ ገዝተኀኛል ፡ በፍቅርህ
ስለእኔ ፡ በደል ፡ ዋጋ ፡ ከፍለሃል
ዛሬ ፡ እኔ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ፡ ያንስሃል
ፍቅርህን ፡ ለመግለጽ ፡ ለእኔ ፡ ሞተሃል
አዝ:- አመልካለሁ ፡ እስከ ፡ ሕይወቴ ፡ ፍጻሜ
ቤትህ ፡ ይሁን ፡ የመጨረሻዬ
አንተን ፡ ትቼ ፡ አማራጭ ፡ አላይም ፡ አላገኝም
ዘለዓለም
ምንም ፡ የለም ፡ ለአንተ ፡ ያደረኩት ፡ ዉለታ
ምላሽ ፡ የሚሆን ፡ ፍቅርህን ፡ የሚተካ
በፊትህ ፡ መቆም ፡ ማይገባኝ ፡ ነበርኩኝ
ግን ፡ በደም ፡ ገዝተህ ፡ ልጅህ ፡ አደረከኝ
አዝ:- አመልካለሁ ፡ እስከ ፡ ሕይወቴ ፡ ፍጻሜ
ቤትህ ፡ ይሁን ፡ የመጨረሻዬ
አንተን ፡ ትቼ ፡ አማራጭ ፡ አላይም ፡ አላገኝም
ዘለዓለም
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ነህ
(ነፍስህን ፡ የሰጠህ) ነፍስህን ፡ የሰጠህ ፡ ስለእኔ
(ራስህን ፡ አዋርደህ) ራስህን ፡ አዋርደህ
አጸዳህ ፡ በደሌን
ስለዚህ ፡ በሕይወት ፡ በኑሮዬ
አንተን ፡ አከብራለሁ
ለዘለዓለም ፡ አሜን
አዝ፦ አመልካለሁ (፱x) (አማራጭ ፡ አላይም ፡ አላገኝም)
ዘለዓለም
አመልካለሁ (፪x) ጌታ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
አመልክሃለሁ (፪x)
|