እጠብቅሃለሁ (Etebeqehalehu) - ዘካሪያስ ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዘካሪያስ ፡ ጌታቸው
(Zekariyas Getachew)

Zekariyas Getachew 1.jpg


(1)

ደረሰልኝ
(Dereselegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዘካሪያስ ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Zekariyas Getachew)

ነገ ፡ መልካም ፡ ይሆናል
እያልኩኝ ፡ በተስፋ ፡ እኖራለሁ
ግራ ፡ ቀኝ ፡ አላይም ፡ እጠብቅሃለሁ (፪x)

ግን ፡ ለምን ፡ አልገባኝም
ስጠራህ ፡ ዝም ፡ አልከኝ
የዓይኖቼ ፡ እምባ ፡ እስኪፈስ
ለምኜ ፡ ተው ፡ ተመለስ (፪x)

በመንፈቅ ፡ ሌሊት ፡ ከአልጋዬ ፡ ወርጄ
ሚስጢሬን ፡ ነገርኩህ ፡ ፊትህ ፡ ተደፍቼ
እንግዲህ ፡ ሁሉንም ፡ በአድራሻ ፡ ልኬያለሁ
እኔም ፡ በአድራሻዬ ፡ እጠብቅሃለሁ (፪x)

ከሰዎች ፡ ደብቄ ፡ ለአንተ ፡ የነገርኩህ
እንዴት ፡ አደረክልኝ ፡ ያጫወትኩህን
ዛሬም ፡ ነገም ፡ እጠብቅሃለሁ
ድንገት ፡ ትመጣለህ ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ (፪x)

ዓመታት ፡ ሲሄዱ ፡ በጥያቄዬ ፡ ላይ
የተውከው ፡ መሰለኝ ፡ ታክቶ ፡ የእኔ ፡ ጉዳይ
ዛሬ ፡ ቢሆን ፡ ነገ ፡ እታገስሃለሁ
ልትረዳኝ ፡ ስትመጣ ፡ ድንገት ፡ አይሃለሁ (፪x)

ከሰዎች ፡ ደብቄ ፡ ለአንተ ፡ የነገርኩህ
እንዴት ፡ አደረክልኝ ፡ ያጫወትኩህን
ዛሬም ፡ ነገም ፡ እጠብቅሃለሁ
ድንገት ፡ ትመጣለህ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ (፪x)

አይሃለሁ ፡ ስትደርስልኝ
አይሃለሁ ፡ ስትመጣልኝ
አይሃለሁ ፡ መልሴንም ፡ ከላይ
አይሃለሁ ፡ ስትልክልኝ (፫x)