አብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም (Abqagn Leyerusalem) - ዛማር ፡ የዝማሬ ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዛማር ፡ የዝማሬ ፡ አገልግሎት
(Zamar Gospel Music Band)


(1)

በደም ፡ ተዋጅተናል
(Bedem Tewajtenal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዛማር ፡ የዝማሬ ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Zamar Gospel Music Band)

አዝአብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም (፫x) ፡ ሕይወቴን
አብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም ፡ ሕይወቴን

በሚያስፈራው ፡ ሞገድ ፡ በሃዘን ፡ ውሽንፍር
መላው ፡ ተደናግሮኝ ፡ ስተክዝ ፡ ስሸበር
ረግረግ ፡ ውስጥ ፡ ሰጥሜ ፡ ጨለማው ፡ ሲውጠኝ
ጠብቀኝ ፡ ጌታዬ ፡ ከጭንቀት ፡ አድነኝ

አዝአብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም (፫x) ፡ ሕይወቴን
አብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም ፡ ሕይወቴን

ሰይጣን ፡ ሲደልለኝ ፡ ዓለምን ፡ እንዳልክድ
አሽከሩ ፡ ሊያደርገኝ ፡ ወጥመዱን ፡ ሲያጠምድ
በዙሪያዬ ፡ ሲዞር ፡ ሲያገሳ ፡ እንደ ፡ አንበሳ
ጠብቀኝ ፡ አምላኬ ፡ ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ አበሳ

አዝአብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም (፫x) ፡ ሕይወቴን
አብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም ፡ ሕይወቴን

መርጫለሁ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ለመከተል
ዓለምን ፡ ንቄአለሁ ፡ ለመሸከም ፡ መስቀል
መከራውን ፡ ችዬ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ልነቀፍ
በጉዞዬ ፡ እርዳኝ ፡ ከእንግዲህ ፡ አምላኬ

አዝአብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም (፫x) ፡ ሕይወቴን
አብቃኝ ፡ ለኢየሩሳሌም ፡ ሕይወቴን