አልዘገየም (Alzegeyem) - ዮሴፍ ፡ ስለሺ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ ስለሺ
(Yoseph Seleshi)

Yoseph Seleshi 1.png


(1)

ህልሜ ፡ ሰፈር ፡ አይቀርም
(Helme Sefer Ayqerem)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ስለሺ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Seleshi)

የህልመኛው ዘመን ጊዜው ደረሰና
ከወህኒው ቤት ወጣ አስቸኮሉትና
እግዚአብሔር ከሰማይ ስላዘነላቸው
ሞቷል የተባለው ነግሶ ጠበቃቸው

አልዘገይም እሄዳለው (2)
ክብር መጥቷል ቅባት መጥቷል እንዴት እቆማለሁ
ወደ ታየልኝ እሄዳለሁ ወደ ታየልኝ
ወደ ነገረኝ እሄዳለሁ ወደ ነገረኝ
x2

ህልሜ ሰፈር አይቀርም ህልሜ (2)
ህልሜ መንደር አይቀርም ህልሜ (2)
በጅምር የሚቀር ህልም የለኝም እኔ (3)
መንገድ ላይ የሚቀር ህልም የለኝም እኔ (3)
ሰፈር ላይ የሚቀር ህልም የለኝም እኔ(3)
ተወርቶ የሚቀር ህልም የለኝም እኔ (3)

ትክክል ነው ያየሁት ትክክል ነው
ትክክል ነው የሰማሁት ትክክል ነው
x2

ማየቴ ለምን አስከፋቸው ጌታ ነው ያሳየኝ ህልሙን
በትንሽነቴ ከፍቶልኝ አይኔን
ጀማሪው ከግብ ያደርሰኛል መንገድ ላይ ማንስ ያስቀረኛል
በጠላቶቼ ፊት ዘይት ቀብቶኛል

ቃል ያለው መቼም አይወድቅም
ቃል ያለው መንገድ አይቀርም
ቃል ያለው መቼም አይወድቅም
ቃል ያለው አውሬ አይበላውም

እንዳልሄድ የከለከለኝን እግሬ ላግ ገመድ አስገብቶ
መንገዴን የዘጋ ወጥመድን ዘርግቶ
እርግማን ታጥቀው ቢሰለፉ አይችሉም እኔን ማዘግየት
ወጥመድ ተሰበረ ሲጨምር ቅባት

ቃል ያለው መቼም አይወድቅም
ቃል ያለው መንገድ አይቀርም
ቃል ያለው መቼም አይወድቅም
ቃል ያለው አውሬ አይበላውም

ህልሜ ሰፈር አይቀርም ህልሜ (2)
ህልሜ መንደር አይቀርም ህልሜ (2)
በጅምር የሚቀር ህልም የለኝም እኔ (3)
መንገድ ላይ የሚቀር ህልም የለኝም እኔ (3)
ሰፈር ላይ የሚቀር ህልም የለኝም እኔ(3)
ተወርቶ የሚቀር ህልም የለኝም እኔ (3)

ትክክል ነው ያየሁት ትክክል ነው
ትክክል ነው የሰማሁት ትክክል ነው
x2

ሄዳለሁ ወደ ከፍታ ይዞኛል የጠራኝ ጌታ x2
ነግሮኛል ሲያስጀምረኝ መንገዴን እንደቀናልኝ x2

ካይኖቼ ላይ ግርዶሽ ገፍፌ አንስቼ
የተሰቀለውን ኢየሱስን አይቼ
እሄዳለሁ እኔማ ኢየሱስን አይቼ
እሄዳለሁ እኔማ መንፈሱን ሰምቼ
እሄዳለሁ እኔማ ኢየሱስን አይቼ
እሄዳለሁ እኔማ ያለኝን ሰምቼ