Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Temechegn Bieteh

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዮሴፍ አያሌው አልበም ሥራዬን የሠራህልኝ

ሥምህ ጋሻዬና ከለላዬ ሆኖልኛል ጌታ በዘመኔ ሳልሰጋ እኖራለው ልቤ እርፎ በኃያሉ ክንድህ ተደግፎ (፪x)

ክበር አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ ንገሥ አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ ግዛኝ አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ

አዝ ተመቸኝ ቤትህ ተመቸኝ ተመችኝ ጉያህ ተመቸኝ

አልመለስም ወደ ኋላ የግብጽን ሽንኩርት ላልበላ ቃልኪዳን ገባሁ ለእራሴ አመልክሃለሁ ኢየሱሴ (፪x)

እንደሚፈስ ዘይት ነው ሥምህ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ እኔም አንተን አንተኑ ብያለሁ ስምህን ላከብር ይሄው ቆሜያለሁ (፪x)

ክበር አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ ንገሥ አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ ግዛኝ አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ

አልመኝ ከአንተ በስተቀር አያምረኝም ያለው በምድር

ቀምሼ አውቄሃለሁ ምርጫዬ አድርጌሃለሁ የሕይወቴ መደምደሚያ ነህ ዘለዓለም ጌታዬ ትበቃኛለህ (፪x)

ክበር አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ ንገሥ አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ ግዛኝ አንተ ብቻ (፪x) የለህ አቻ

አዝ ተመቸኝ ቤትህ ተመቸኝ ተመችኝ ጉያህ ተመቸኝ

አልመለስም ወደ ኋላ የግብጽን ሽንኩርት ላልበላ ቃልኪዳን ገባሁ ለእራሴ አመልክሃለሁ ፡ ኢየሱሴ (፪x)