Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Tedegefiewalehu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ዮሴፍ አያሌው አልበም ሥራዬን የሠራህልኝ

አሃሃ ለሚመኩበት አሃሃ ጋሻ ይሆናል አሃሃ ተስፋ ላደረጉት አሃሃ መች ያሳፍራል (፪x)

መታመኛዬ ቸሩ ጌታዬ ነገን አልፈራም ምን ይሆን ብዬ ምን ይሆን ብዬ (፪x)

ደመናን አይቼ ይዘንባል አልልም ጐተራዬ ሞልቷል ብዬ አልደገፍም (፪x)

መታመኛዬ ቸሩ ጌታዬ ነገን አልፈራም ምን ይሆን ብዬ ምን ይሆን ብዬ (፪x)

ተደግፌዋለሁ አሃሃ ታምኜበታለሁ ኦሆሆ (፬x) ይታመናል ጌታ ይታመናል ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)

አይሸነጋጋልም እውነት ይናገራል ያለውን ሊፈጽም በቃሉ ይተጋል (፪x)

መታመኛዬ ቸሩ ጌታዬ ነገን አልፈራም ምን ይሆን ብዬ ምን ይሆን ብዬ (፪x)

አሃሃ ሃሰትን አያውቅ አሃሃ ቃሉ እውነተኛ አሃሃ ያለውን ሊያደረግ አሃሃ ታማኝ ነው ጌታ (፪x) ይታመናል ጌታ ይታመናል ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)

ተደግፌዋለሁ አሃሃ ታምኜበታለሁ ኦሆሆ (፬x) ይታመናል ጌታ ይታመናል ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)

አልፋና ኦሜጋ ጌታ ኤልሻዳይ ነው ዛሬም ሊሚጠሩት እርሱ ሁሉን ቻይ ነው (፪x)

የሚያኮራ ነው የሚያስተማምን ጌታን የያዘ ከቶ ምን ሊሆን እስኪ ምን ሊሆን (፪x)

አሃሃ ዘለዓለም ነዋሪ አሃሃ እርጅና አያውቀው አሃሃ አልፋና ኦሜጋ አሃሃ እርሱ ብቻ ነው (፪x)

ይታመናል ጌታ ይታመናል ይታመናል ኢየሱስ ይታመናል (፫x)