From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ
ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x)
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x)
ፍቅሩ ፡ አይቀዘቅዝ ፡ ወረት ፡ አያውቀው
እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ አይገኝም
የተናገረውን ፡ ቃሉ ፡ ይፈጽማል
ተናግሮ ፡ ማድረግ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል
አዝ፦ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ
ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x)
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x)
ማክበርና ፡ ማንሳት ፡ ጌታ ፡ ያውቅበታል
እርሱን ፡ የተጠጋ ፡ የቱ ፡ መሽቶበታል
እንደ ፡ ንጋት ፡ ብርሃን ፡ ክብሩ ፡ እየጨመረ
አቀማጥሎ ፡ ያኖራል ፡ እንዲህ ፡ እያከበረ
አዝ፦ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ
ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x)
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x)
የቱነው ፡ የተረሳ ፡ ማነው ፡ የሚጸጸት
ሳይታሰብ ፡ ኖሮ ፡ ጊዜው ፡ ያለፈበት
የተጣለው ፡ ይልቅ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርጐ
ደስታ ፡ ይሰጠዋል ፡ እንባን ፡ ከዓይኑ ፡ ጠርጐ
አዝ፦ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ
ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x)
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x)
አይጠረጠርም ፡ ይታመናል ፡ እንጂ
እንኳን ፡ ቤቱ ፡ ኖሮ ፡ አድጐ ፡ በእርሱ ፡ እጂ
ያሳልፍለታል ፡ ዘመኑን ፡ በተድላ
እርዳኝ ፡ ብሎ ፡ መጥቶ ፡ የቱ ፡ ሰው ፡ ተጐዳ
አዝ፦ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ
ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x)
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x)
|