Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Serayien Yeserahelegn
ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ
ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ
አማኑኤል ከፍ በልልኝ
አማኑኤል ከፍ በልልኝ
ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ
የእኔ ጌታ ከፍ በልልኝ
ተራራውን ንዶ ሜዳ ካደረገው
መራመድ ብቻ ነው ከእኔ ሚጠበቀው
ተራራውን ንዶ ሜዳ ካደረገው
መራመድ ብቻ ነው ከእኔ ሚጠበቀው
ጐዳናዬ ቀንቶ ተራመድ ብሎኛል
ከእኔ ጋር ስላለ ማን ይቃወመኛል
ጐዳናዬ ቀንቶ ተራመድ ብሎኛል
ከእኔ ጋር ስላለ ማን ይቃወመኛል
ማን ይቃወመኛል
ማን ይቃወመኛል
የቱ ይይዘኛል
የቱ ይይዘኛል
አልፈራም ልቤ አይሰጋ ጌታዬ አለ ከእኔ ጋ
አልፈራም ልቤ አይሰጋ የጠራኝ አለ ከእኔ ጋ
አይቆምም ምንም ከፊቴ እግዚአብሔር ነው ዛሬም ጉልበቴ
እግዚአብሔር ነው ዛሬም ጉልበቴ (4)
ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ (2)
አማኑኤል ከፍ በልልኝ (2)
ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ
የእኔ ጌታ ከፍ በልልኝ
ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊት ወጥቷልና
ሃሳቤ ተሳክቶ መንገዴም ተቃና
ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊት ወጥቷልና
ሃሳቤ ተሳክቶ መንገዴም ተቃና
የነሃሱን ደጆች በስልጣን ሰበረው
እኔም ሰባብሬ ከእርሱ ጋር አልፌያለው
ከእርሱ ጋር አልፌያለው(4)
አልዝልም እኔ አልደክምም ስራዬ አያሰለችም
አልዝልም እኔ አልደክምም ስራዬ አያሰለችም
ቅባቱ በእኔ ስላለ ይሄዳል እየጨመረ
ይሄዳል እየጨመረ(4)
ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ....
ታማኝ ነው የጠራኝ ጌታ ለምንም ትጥቄ አይፈታ
ታማኝ ነው የጠራኝ ጌታ ለምንም ትጥቄ አይፈታ
ብርቱ ነው በቃሉ የፀና ይመራኛል በድል ጐዳና
ይመራኛል በድል ጐዳና(4)
ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ....
ከፍ በል ብል ሁልጊዜ ይሄ መች ይበቃሃል ይሄ መች ይበቃሃል ይሄ መች ይበቃሃል
ተባረክ ብል ሁልጊዜ ይሄ መች ይበቃሃል ይሄ መች ይበቃሃል ይሄ መች ይበቃሃል
ተመለክ ብል ሁልጊዜ ይሄ መች ይበቃሃል ይሄ መች ይበቃሃል ይሄ መች ይበቃሃል