From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ላይጨልምብኝ ፡ አንዴ ፡ አብርቶት ፡ ጌታ ፡ ነገሩን ፡ ሁሉ ፡ ገልብጦ (፪x)
ያለፈውን ፡ እንዳላስበው ፡ እንቅፋቶቹን ፡ አነሳሳቸው (፪x)
ጨለማዬን ፡ አበራኸው ፡ እንደፈሳሽ ፡ አሳለፍከው
ጐህ ፡ ቀደደ ፡ ቀን ፡ ሊወጣ ፡ ማረፊያዬ ፡ ዘመን ፡ መጣ
መኖሪያዬ ፡ አንተ ፡ ሆንክልኝ ፡ ከጭንቀቴ ፡ አሳለፍከኝ/ገላገልከኝ (፪x)
ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተባረክ (፪x)
እስኪ ፡ ደጋግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው
እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ ስላላየሁ
ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን
ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ነኝ
ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር ፤ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር (፪x)
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x)
ከፊት ፡ ከፊቴ ፡ ጌታዬ ፡ ወጣና
እሾሁን ፡ ሁሉ ፡ አነሳሳና (፪x)
አደላደለው ፡ ሕይወቴ ፡ ቀና
ይመራኝ ፡ ጀመር ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x)
እረዳቴ ፡ ሆነህልኝ ፡ ተሸክመህ ፡ አሻገርከኝ
አልነደፈኝ ፡ እባብ ፡ ጊንጡ
መች ፡ አገኘን ፡ እንደ ፡ ምኞቱ
ከፍ ፡ ላድርግህ ፡ ቸር ፡ ጌታዬ
ደስ ፡ ያሰኝህ ፡ ምሥጋናዬ (፪x)
ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተባረክ (፪x)
እስኪ ፡ ደጋግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው
እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ ስላላየሁ
ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን
ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ነኝ
ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር ፤ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር (፪x)
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x)
ያ ፡ ደመና ፡ እንዳያልፍ ፡ የለም ፡ ሲያስገመግም
ጠላቴም ፡ ሲለኝ ፡ የሚያድንህ ፡ የለም
ኧረዳቴ ፡ ግን ፡ እጁን ፡ ዘረጋ ፡ ከሰማያት
እኔን ፡ ሊያወጣ ፡ ፈጥኖ ፡ ከሞት
አንተ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ጌታ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ
ኢየሱስ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ
ምን ፡ ልበልህ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ልበልህ
ምን ፡ ልበልህ ፡ ጌታዬ ፡ ምን ፡ ልበልህ
ምን ፡ ልክፈልህ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ
|