From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (፪x)
በስራው ፡ የበረታ ፡ ማዳኑ ፡ ወደር ፡ የለው
ጌታዬ ፡ ወደር ፡ የለው (፪x)
አደርጋለሁ ፡ እንዳለ ፡ እንዲሁ ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ነው
እንዲሁ ፡ እንደቃሉ ፡ ነው ፤ እንዲሁ ፡ እንደቃሉ ፡ ነው (፪x)
አስገርሞኛል ፡ ትላቅነቱ ፡ እዘምራለው ፡ ለጌትነቱ (፪x)
አዝ፦ እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (፪x)
ሞትን ፡ የሰባበረ ፡ ሲኦልን ፡ ድል ፡ የነሳው
ሲኦልን ፡ ድል ፡ የነሳው (፫x)
ዛሬ ፡ ከመቃብር ፡ በላይ ፡ ስሙ ፡ የሚዘከረው
ስራው ፡ የሚነገረው ፤ ስራው ፡ የሚነገረው (፪x)
የትንሳኤ ፡ አምላክ ፡ ድንቅ ፡ አድራጊ ፡ ነህ
በፈጠርካቸው ፡ ትመለካለህ (፪x)
አዝ፦ እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (፪x)
የሃያላኖች ፡ ሃያል ፡ ስሙ ፡ ነው ፡ የከበረ
ስሙ ፡ ነው ፡ የከበረ (፪x)
ሁሉን ፡ በስልጣኑ ፡ ቃል ፡ አቆመ ፡ እየደገፈ
አቆመ ፡ እየደገፈ ፤ አቆመ ፡ እየደገፈ (፪x)
የሰማይ ፡ የምድር ፡ ሁሉ ፡ ፈጠሪ
ዘመኑ ፡ አያልቅ ፡ ዘለዓለም ፡ ነዋሪ (፪x)
አዝ፦ እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (፪x)
አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ሆይ ፡ ዙፋንህ ፡ የጸና
ዙፋንህም ፡ የጸና (፪x)
ዘመናት ፡ አይለውጡህ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ገናና
ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ገናና ፤ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ገናና (፪x)
አይገረሰስ ፡ ጸኑ ፡ መንግሥትህ
እርጅና ፡ አያውቀው ፡ የአንተ ፡ አገዛዝህ (፪x)
አዝ፦ እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (፪x)
|