Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Anten Keyaze Sew
ዘማሪ ዮሴፍ አያሌው ርዕስ አንተን ከያዘ ሰው አልበም ሥራዬን የሠራህልኝ
አዝ አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (፪x)
አባትስ ማለት እንደ አንተ ነው ወዳጅስ ማለት እንደ አንተ ነው አሳድገኽኛል ከእጅህ እየበላሁ ሰው የሆንኩት በአንተ ነው ይህንን ልቤ አልረሳው (፬x)
አዝ አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (፪x)
ዘመን ሲከፋ ሲቀያየር አንተ ግን ያው ነህ እግዚአብሔር ፀጋህ አልጐደለ ለእኔ ለልጅህ ቤትህ ያገባኛል አባብሎ ምህረትህ (፬x)
አዝ አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (፪x)
አትለዋወጥ ጠዋት ማታ ፊትህ አይጠቁር የእኔ ጌታ አልቆረቆረኝም ትከሻህ ጌታዬ ተመችተኽኛል አንተ ነህ አለኝታዬ (፬x)
አዝ አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) (ኦ ምን ይሆናል) አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (፪x)
ሰማይ ምድርንም ትገዛለህ የፈቀድከውን ታደርጋለህ አንዳች አላጣሁም በስምህ ለምኜ ፊቴ አላፈረም እጅህን ታምኜ (፬x)
አዝ አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆና (፫x) (ኦ ምን ይሆናል) አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል (፫x) የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (፪x)