ወዶኛል ፡ እና ፡ አዳነኝ (Wedognal Ena Adanegn) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg


(3)

ስንቱን ፡ ላውራ
(Sentun Lawra)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

ቸርነቱን ፡ ለእኔ ፡ ሁሌ ፡ እዘምራለሁ
የአባትነት ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ስላየሁ
ጐልጐታ ፡ አናት ፡ ላይ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶልኛል
የኀጢአት ፡ እስራቴን ፡ በጥሶ ፡ ጥሎታል (፪x)

አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x)
ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x)
ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x)
ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x)

ከሰማይ ፡ ሰማያት ፡ ከዙፋኑ ፡ ወርዶ
ሁሉን ፡ ስለፍቅር ፡ አደረገ ፡ ባዶ
መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ያለው
ያ ፡ ሁሉ ፡ ስቃዩ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x)
ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x)

አደባባይ ፡ ቆመ ፡ እርቃኑን ፡ ስለ ፡ እኔ
አላፈረብኝም ፡ ኢየሱስ ፡ መድኅኔ
በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ሞቶ ፡ እኔን ፡ አድኖኛል
በከበረው ፡ ደሙ ፡ ጌታዬ ፡ ዋጅቶኛል (፪x)

አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x)
ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x)

የምህረት ፡ መግቢያ ፡ በሩ ፡ ተክፈተ
የጥሉ ፡ ግድግዳ ፡ በደሙ ፡ ፈረሰ
ተፈጸመ ፡ ብሎ ፡ ሁሉን ፡ ጨርሶታል
ሞትና ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነስቶ ፡ ተነስቷል (፪x)

አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x)
ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፮x)