ማነው ፡ ታማኝ ፡ አገልጋይ (Manew Tamagn Agelgay) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg


(3)

ስንቱን ፡ ላውራ
(Sentun Lawra)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

 
በምድራዊው ፡ ጥቅም ፡ ነፍሱ ፡ ያልታሰረ
ክቡሩን ፡ አደራ ፡ በስራ ፡ ያዋለ
እራሱን ፡ ሸሽጐ ፡ አምላኩን ፡ ሚያሳይ
ማነው ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ እውነተኛ ፡ አገልጋይ (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ታማኝ ፡ አገልጋይ ፤ ማነው ፡ ትጉህ ፡ ኧረኛ
ማነው ፡ ልባም ፡ መጋቢ ፤ ማነው ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ማነው ፡ ፍቅርን ፡ የተሞላ ፤ ማነው ፡ ደግሞም ፡ የጸሎት ፡ ሰው
ማነው ፡ ለነፍሳት ፡ አሳቢ ፤ ማነው ፡ እውነት ፡ የሚገደው
እንዲህ ፡ ሲያደርግ ፡ ለሚገኘው
ከአምላኩ ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ ፡ አለው

ከጊዜያዊው ፡ ይልቅ ፡ ሚበልጠውን ፡ ሽቶ
ዘለዓለማዊውን ፡ ከሩቅ ፡ ተመልክቶ
ትኩር ፡ ብሎ ፡ ያየ ፡ ያንን ፡ ብድራቱን
በጌታው ፡ ያረፈ ፡ እውነተኛ ፡ ካህን (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ታማኝ ፡ አገልጋይ ፤ ማነው ፡ ትጉህ ፡ ኧረኛ
ማነው ፡ ልባም ፡ መጋቢ ፤ ማነው ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ማነው ፡ ፍቅርን ፡ የተሞላ ፤ ማነው ፡ ደግሞም ፡ የጸሎት ፡ ሰው
ማነው ፡ ለነፍሳት ፡ አሳቢ ፤ ማነው ፡ እውነት ፡ የሚገደው
እንዲህ ፡ ሲያደርግ ፡ ለሚገኘው
ከአምላኩ ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ ፡ አለው

ነውረኛውን ፡ ነገር ፡ ጸያፉን ፡ የናቀ
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ዝና ፡ እራሱን ፡ ያራቀ
ቅድስናን ፡ ለብሶ ፡ ለጌታው ፡ የሚኖር
እግዚአብሔር ፡ የጠራው ፡ ማነው ፡ አምባሳደር (፪x)

እርዳኝ ፡ አባቴ ፡ ኦሆሆሆሆ
አግባኝ ፡ ከቤቴ ፡ በሰላም
(፬x)