ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው (Kehulu Belay New) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg


(3)

ስንቱን ፡ ላውራ
(Sentun Lawra)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

 
እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው
ማነው ፡ የሚመስለው ፡ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው
ማነው ፡ የሚያክለው ፡ እርሱ ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አዎ

አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x)

በምድር ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ገነው ፡ የነበሩ
እጅግ ፡ የከበሩ ፡ ደግሞም ፡ የተፈሩ
ብርቱ ፡ ሃያላኖች ፡ ጠቢባን ፡ ወድቀዋል
ብዙዎች ፡ ነገሥታት ፡ ወድቀው ፡ ተረስተዋል

የእኛ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ዛሬም ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ጉልበቱ ፡ ሳይደክም ፡ አለ ፡ በዙፋኑ ፡ በዙፋኑ
አለ ፡ በዙፋኑ ፡ አዎ
መቃብር ፡ ፈንቅሎ ፡ ድል ፡ ነስቶ ፡ የተነሳ
እርሱ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ አዎ

አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፫x)

ናቡከደነጾር ፡ ምስል ፡ አሰራና
ስገዱ ፡ አላቸው ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ አለና
ለምስሉ ፡ ከቶ ፡ አንሰግዱም ፡ ያሉ
እነሲድራቅ ፡ ታስረው ፡ በእቶኑ ፡ ተጣሉ
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ሆኖ ፡ ቢነድም ፡ እሳቱ
እርሱን ፡ የታመኑ ፡ አሸንፈው ፡ ወጡ ፡ ሃሌሉያ
ድል ፡ አድርገው ፡ ወጡ [1]
የነሲድራቅ ፡ አምላክ ፡ አሁንም ፡ ይሰራል
ስሙን ፡ ለሚጠራው ፡ ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ሃሌሉያ
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ አዎ

ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አሃ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኦሆ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ጌታ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ጌታ (፫x)

በጸናችው ፡ እጁ ፡ ህዝቡን ፡ አወጣቸው [2]
ባሕሩን ፡ አሻግሮ ፡ በድንቅ ፡ መራቸው [3]
ከኋላም ፡ ከፊትም ፡ ሆኗቸው ፡ ከለላ
ተስፋውን ፡ ወረሱ ፡ ቃሉንም ፡ አጸና [4]

ለእኔማ ፡ አባቴ ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ አምነዋለሁ
ቢጐድልም ፡ ቢሞላም ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
በቁሳቁስ ፡ ነገር ፡ እኔ ፡ አልመዝነውም
ከሁሉም ፡ ይልቃል ፡ ጌታ ፡ እኩያ ፡ የለውም ፡ አባብዬ
እኩያ ፡ የለውም ፡ አዎ

አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፫x)

እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (በዙፋኑ ፡ ላይ)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (ኦ ፡ ላይ ፡ ነው)
ማነው ፡ የሚመስለው (የእኔ ፡ ጌታ) ፡ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (ማነው ፡ ማነው)
ማነው ፡ የሚያክለው (ኢየሱሴን) ፡ እርሱ ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ (አዎ ፡ አዎ)

አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ (በላይ ፡ በላይ)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (በላይ ፡ ነው)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (በላይ ፡ በላይ)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፫x)

  1. ዳንኤል ፫ (Daniel 3)
  2. ዘጸአት ፲፪ ፡ ፴፩ - ፴፮ (Exodus 12:31-36)
  3. ዘጸአት ፲፬ ፡ ፲፭ - ፴፩ (Exodus 14:15-31)
  4. ኢያሱ ፮ (Joshua 6)