ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (Gieta Eko Neh) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg


(3)

ስንቱን ፡ ላውራ
(Sentun Lawra)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

አዝ፦ ካለመኖር ፡ ወደመኖር ፡ ታመጣለህ
ቃል ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ምንተስኖህ ፡ ትሰራለህ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)
አባቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)

በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ነፍስ ፡ ህይወትን ፡ ዘርተህ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
ታኖራለህ ፡ ጌታ ፡ መቃብርን ፡ ከፍተህ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ስትሽር ፡ አይቻለሁ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
ታሪክ ፡ ተገልብጦ ፡ እንዲህ ፡ እዘምራለሁ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))

ጨለማ ፡ በፊቴ ፡ አይጨልምም
ጌታ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም
እኔማ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ከሞት ፡ ያመለጥኩት ፡ በአንተ ፡ እኮ ፡ ነው
ጌታ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ ፡ መታመኛዬ ፡ አዎ
ጌታ ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩት ፡ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ትምኜው

አዝ፦ ካለመኖር ፡ ወደመኖር ፡ ታመጣለህ
ቃል ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ምንተስኖህ ፡ ትሰራለህ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)
አባቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)

እንደማያልፍ ፡ የለም ፡ አለፈ ፡ በተራ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
እንደፈሳሽ ፡ ውኃ ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ መከራ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
በዚያ ፡ ክፉ ፡ ሌሊት ፡ ደርሰህ ፡ አሳረፍከኝ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
ባለውለታዬ ፡ አንተው ፡ ክበርልኝ (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))

አዝ፦ ካለመኖር ፡ ወደመኖር ፡ ታመጣለህ
ቃል ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ምንተስኖህ ፡ ትሰራለህ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)
አባቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)

ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ በዓልጋው ፡ ለነበረው (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
ዘመን ፡ መጥቶለታል ፡ ለዚያ ፡ ለሽባው ፡ ሰው (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
እስርአቱን ፡ ፈተህ ፡ አዘልለኸዋል (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))
አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳናል (ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x))

ጨለማ ፡ በፊቴ ፡ አይጨልምም
ጌታ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም
እኔማ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ከሞት ፡ ያመለጥኩት ፡ በአንተ ፡ እኮ ፡ ነው
ጌታ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ ፡ መታመኛዬ ፡ አዎ
ጌታ ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩት ፡ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ትምኜው

አዝ፦ ካለመኖር ፡ ወደመኖር ፡ ታመጣለህ
ቃል ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ምንተስኖህ ፡ ትሰራለህ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)
አባቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)