አላማዬ ፡ ነው (Alamayie New) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg


(3)

ስንቱን ፡ ላውራ
(Sentun Lawra)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)

 
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አላማዬ ፡ ነዉ (፪x)
ጠላት ፡ የሚለኝን ፡ ለምንስ ፡ ልስማዉ
ልውጣ ፡ ልሄድ ፡ ልውረሰዉ ፡ አዎ (፪x)

አላማ ፡ ያላቸው ፡ የጥንት ፡ አባቶቼ
ድል ፡ አደረጉ ፡ እንጂ ፡ ተሸነፉ ፡ መቼ
እኔም ፡ አላማዬን ፡ አንተን ፡ አድርጌያለሁ
የጠላቶቼን ፡ ደጅ ፡ በእምነት ፡ እወርሳለሁ
እወርሳለሁ ፤ እወርሳለሁ (፬x)

አማሌቅ ፡ በፊቴ ፡ ሆኖ ፡ ቢያቅራራ
ምን ፡ ትልቅ ፡ ቢመስል ፡ እኔ ፡ እንደው ፡ አልፈራ
የአምላኬን ፡ ስም ፡ ይዤ ፡ በእምነት ፡ እወጣለሁ
ጠላቴን ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ አጋድመዋለሁ
አምላኬ ፡ ሃይሌ ፡ ነው
እኔ ፡ አልፈራም ፡ አልፈራም (፪x)
እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አልሰጋም (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አላማዬ ፡ ነዉ (፪x)
ጠላት ፡ የሚለኝን ፡ ለምንስ ፡ ልስማዉ
ልውጣ ፡ ልሄድ ፡ ልውረሰዉ ፡ አዎ (፪x)

እንደ ፡ ሰናኦር ፡ ግምብ ፡ ቢቆምም ፡ በፊቴ
ይደባልቀዋል ፡ ቋንቋውን ፡ አባቴ
ምርኮን ፡ በምርኮ ፡ ላይ ፡ ይጨምርልኛል
ያመንኩት ፡ ጌታዬ ፡ መቼ ፡ ይተወኛል (፪x)
እኔ ፡ አልፈራም ፡ አልፈራም (፪x)
እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አልሰጋም (፪x)

የድል ፡ ሰንደቄ ፡ ነው ፡ የሕይወቴ ፡ አርባ ፡ አሃሃ
እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታ ፡ ባለግርማ
ባለግርማ ፡ ኢየሱስ ፡ ባለግርማ (፪x)