ዙሪያየ ሲጨልምብኝ (Abietu Endante manew) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yoseph Bekele)

Lyrics.jpg

(3)

ስንቱን ፡ ላውራ
(Sentun Lawra)

ዓ.ም. (Year): (2017)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:16
ጸሐፊ (Writer):
(BAlex Tube
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yoseph Bekele)
https://www.youtube.com/watch?v=18KJy0-ell8

ዙሪያየ ፡ ሲጨልምብኝ ፡ መሄጃ ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ
ዓይኖቼን ፡ ወደአንተ ፡ አቀናሁ ፡ አባባ ፡ ፍጠንልኝ ፡ አልሁኝ
አንተም ፡ አንጐዳጐድክና ፡ ጠላቴንም ፡ በተንክና
ዳግም ፡ አጽንተህ ፡ አቆምከኝ ፡ ብርቱ ፡ ጦርኛም ፡ አረከኝ

በሀዝን ፡ ችግሬ ፡ ጊዜ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ደራስሽ ፡ አጋዤ
ስጠራህ ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ፡ ሳነባ ፡ እንባዬን ፡ ምታብስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ (ኢየሱስዬ) ፡ እንዳንተ ፡ ማነው(፪x)

ጠላቴ ፡ ወጥመድ ፡ ዝርግቶ ፡ በብርቱ ፡ ነፍሴን ፡ ፈልጐ
ዙሪያዬን ፡ ሲዞር ፡ ሲያደባ ፡ ሲዶልት ፡ ከጁ ፡ ሊያስገባ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ በቅን ፡ የምትፈርድ
ወጥመዱን ፡ ሰባበርክልኝ ፡ ከለላ ፡ አንባዬ ፡ ሆንክልኝ

በሀዝን ፡ ችግሬ ፡ ጊዜ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ደራስሽ ፡ አጋዤ
ስጠራህ ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ፡ ሳነባ ፡ እንባዬን ፡ ምታብስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ (ኢየሱስዬ) ፡ እንዳንተ ፡ ማነው(፪x)

በምክርህ ፡ አንተ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ በፍቅር ፡ የያዝህ
ምሬቴን ፡ ከእኔ ፡ አውጥተሃል ፡ በፍቅር ፡ ቃል ፡ አጽናንተኸኛል
የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ ያበራህ ፡ ቅጥቅጥ ፡ ሸንበቆዬን ፡ ያጸናህ
እንዳንተ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ልክፈል ፡ ለአንተስ ፡ ውለታ

በሀዝን ፡ ችግሬ ፡ ጊዜ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ደራስሽ ፡ አጋዤ
ስጠራህ ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ፡ ሳነባ ፡ እንባዬን ፡ ምታብስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ (ኢየሱስዬ) ፡ እንዳንተ ፡ ማነው(፪x)

እንዳንተ ፡ ማንው ፡ ማ ፡ ነው?
እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ ኢየሱስ(ለእኔ ፡ የደረሰ)
(፪x)

አንተን ፡ ብዬ ፡ ስምህን ፡ ጠርቼ
መች ፡ አፍሬ ፡ አውቃለሁ ፡ ጌታ
አመልክሃለሁ ፡ ጥዋት ፡ ማታ

[አመልክሃለሁ(፫x)](፪x)