ይሰራል (Yeseral) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ለእግዚአብሔር ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ
የሚያቅተው ፡ አለ ፡ ወይ
አለ ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አለ ፡ ወይ
ለኢየሱስ ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ
የሚያቅተው ፡ አለ ፡ ወይ
አለ ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አለ ፡ ወይ

በፍፁም ፡ የለም ፡ አልሰማሁም
ከትላንት ፡ ዛሬም ፡ አላየሁም
እኔ ፡ የገባኝ ፡ አንድ ፡ እውነት
የእግዚአብሔር ፡ ታላቅነት

ይሰራል ፡ ዛሬም ፡ ይሰራል
ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
አምናለሁ ፡ እኔ ፡ አይቻለሁ
ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው (፪x)
ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለጌታ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው

አበቃ ፡ ከእንግዲህ ፡ ለተባለ ፡ ሁሉ
ሲያኖር ፡ አይቻለሁ ፡ በሕይወት ፡ እንደቃሉ
መቃብር ፡ ከፍቶ ፡ የሞተን ፡ ያስነሳል
እኔ ፡ የማመልከው ፡ አምላኬ ፡ ይሰራል
አምላኬ ፡ ይሰራል ፡ አምላኬ ፡ ይሰራል
አባቴ ፡ ይሰራል ፡ አባቴ ፡ ይሰራል

ይሰራል ፡ ዛሬም ፡ ይሰራል
ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
አምናለሁ ፡ እኔ ፡ አይቻለሁ
ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለጌታ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው

ነፍሴን ፡ የፈጠረ ፡ ያበጀ ፡ ሥጋዬን
ሕያው ፡ ያደረገኝ ፡ ሰጥቶ ፡ እስትንፋስን
ይችላል ፡ ወይ ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ ልጠርጥረው
እኔ ፡ ልመን ፡ እንጂ ፡ ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው
ለአባቴ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ለኢየሱስ ፡ ቀላል ፡ ነው

ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለኢየሱስ ፡ ይቻላል (፪x)
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአባቴ ፡ ይቻላል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለጌታ ፡ ይቻላል
ለኢየሱስ ፡ ይቻላል ፡ ለኢየሱስ ፡ ይቻላል
ለጌታ ፡ ይቻላል ፡ አዎ ፡ ይቻላል
ይቻላል ፡ ይቻላል ፡ ኦሆ ፡ ይቻላል ፡ ይቻላል

ሟርተኛው ፡ ቢያሟርት ፡ አይሁንለት ፡ ብሎ
ሊያዘገይ ፡ ቢሞክር ፡ በረከቴን ፡ ታግሎ
በአምላኬ ፡ ስም ፡ ሆኜ ፡ አሸንፈዋለሁ
የኢየሱስ ፡ ስሙ ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው
ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው
ምሽግን ፡ ለማፍረስ ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው

ነፋስ ፡ ባይታይ ፡ ደመና
ጭው ፡ ያለ ፡ ቢሆን ፡ በረሃ
እኔስ ፡ አባቴን ፡ አውቀዋለሁ
እንደሚሰራ ፡ አምነዋለሁ

አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ
ጐዶሎው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ
አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ
የሌለው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ
አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ ጐዶሎው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ
አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ የሌለው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ (፪x)