የማዕዘን ፡ ራስ (Yemaezen Ras) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ኢየሱስ ፡ ከስም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስሙ ፡ ኃያል
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ፊቱ ፡ ተንበርክኮ ፡ ለእርሱ ፡ ይሰግዳል
አይቆምም ፡ ማንም ፡ ፊቱ ፡ እሳት ፡ ነው ፡ ለጠላቱ
አምላኬ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ኢየሱስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፤ የሱሴ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ጌታዬ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፤ ኢየሱሴ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ

አሃ ፡ ለተቀበሉት ፡ አሃ ፡ በእርሱ ፡ ለሚያምኑት
የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው
ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፤ ኢየሱስ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው
ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፤ አሃ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው

ግንበኞች ፡ የናቁት ፡ ድንጋይ
እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ ፡ ሆነ
እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ
እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ ፡ ሆነ
እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ

ከስም ፡ በላይ ፡ ስምን ፡ ሰጥቶ
እግዚአብሔር ፡ ያለልክ ፡ ያከበረው
ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ጌታዪ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ንጉሤ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ አባቴ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ አዳኜ ፡ ነው

ያድናል ፡ የሚጠራውን ፡ ያድናል ፡ የታመነውን
ያድናል ፡ በልቡ ፡ ዙፋን ፡ ያድናል ፡ ያነገሠውን

ኢየሱስ ፡ ከሞት ፡ የማምለጫ ፡ ጽኑ ፡ አለት
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ስሙን ፡ እየጠራ ፡ ሚድንበት
ሕይወት ፡ ነው ፡ የዘለዓለም ፡ የሚያድን ፡ ከጠፊው ፡ ዓለም
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም
ሕይወት ፡ ነው ፡ የዘለዓለም ፡ ከእሱ ፡ በቀር ፡ አዳኝ ፡ የለም
ንጉሥ ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ፡ አዳኝ ፡ የለም

አሃ ፡ ለተቀበሉት ፡ አሃ ፡ በእርሱ ፡ ለሚያምኑት
የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው
ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፡ ኢየሱስ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው
ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፡ አሃ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው

ይሄ ፡ ስም ፡ ነው ፡ መዳኛዬ
በክፉ ፡ ቀን ፡ ማምለጫዬ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መዳኛዬ
በክፉ ፡ ቀን ፡ ማምለጫዬ (፫x)

ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ
ሾሜዋለሁ ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ እኔስ ፡ በላዬ ፡ ላይ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ (ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ) (፮x)