ይሆናል (Yehonal) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

የቀድሞውን ፡ ነገር ፡ አላስብም
አሮጌው ፡ ሁሉ ፡ አልፏል ፡ ሁሉ ፡ አልፏል
ተፈጠመ ፡ ያየጥንቱ ፡ ታሪክ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል
የቀድሞውን ፡ ነገር ፡ አላስብም
አሮጌው ፡ ሁሉ ፡ አልፏል ፡ ሁሉ ፡ አልፏል
የእንባው ፡ ጊዜ ፡ ታሪክ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር ፡ ቀን ፡ ተቀጥሮለታል

እነሆ ፡ ሁሉን ፡ አዲስ ፡ አደርጋለሁ
እርሱንም ፡ አሁን ፡ አበቅለዋለሁ
ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ያለኝ ፡ ጌታ
የተናገረኝን ፡ ያደርገዋል ፡ ያደርገዋል ፡ አምነዋለሁኝ
አምነዋለሁኝ (፬x)

ይሆናል ፡ አዲስ ፡ ነገር
አያለሁ ፡ አንድም ፡ አይቀር
ይሆናል ፡ አዲስ ፡ ነገር
አያለሁ ፡ አንድም ፡ አይቀር

የተናገረኝ ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ አይደል ፡ ሚያመነታ
ቃል ፡ ወጥቷልና ፡ ከእርሱ ፡ ያደርገዋል ፡ ንጉሡ

ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ ጌታ ፡ ያለው ፡ ይሆናል
ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ እርሱ ፡ ያለው ፡ ይሆናል

(አዲስ ፡ ነገር ፡ ይሆናል ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ነገር)

ሽንፈት ፡ አላወራም ፡ ድል ፡ አለ ፡ ከፊቴ
ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ትምክቴ
የነሃሱ ፡ ደጃፍ ፡ አውቆ ፡ ይከፈታል
እግዚአብሔር ፡ ሲነሳ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ይቆማል

ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ይሆናል
ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ እርሱ ፡ ያለው ፡ ይሆናል

ዐይኖች ፡ ያላዩትን ፡ ጆሮም ፡ ያልሰማውም
ከሰዎች ፡ ዘንድ ፡ ከቶ ፡ ያልተገመተውን
እንግዳ ፡ ነገርን ፡ አምላኬ ፡ ያደርጋል
አዲስ ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ ይሆናል

ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ
ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ
ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ
ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ
አያለሁ ፡ በዐይኔ (፬x)

ምድረ ፡ በዳ ፡ ቢሆን ፡ አንተ ፡ ያለህበት
አትፍራ ፡ ወንድሜ ፡ ጽና ፡ በቆምክበት
ጻድቁ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዴት ፡ ይጥልሃል
ታሪክን ፡ ገልብጦ ፡ ገና ፡ ያቆምሃል

ተስፋ ፡ የሰጠህ ፡ የታመነው ፡ የታመነው
ሁሉን ፡ ይሰራል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው
ተስፋ ፡ የሰጠህ ፡ የታመነው ፡ የታመነው
ሁሉን ፡ ይሰራል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው

አምናለሁ ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ይሰራል ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ያደርጋል ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው

ምድር ፡ ብታልፍ ፡ ሠማይ ፡ ቢያልፍ
ቃሌ ፡ ግን ፡ አያልፍም ፡ ያለው
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፪x)

ኧረ ፡ የምን ፡ ሥጋት ፡ ለምን ፡ ፍርሃት
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ አምላክ
አለኝ ፡ አባት
ትዕዛዝ ፡ ከሠማይ ፡ ከአምላኬ ፡ ወጥቶ
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ ከቶ
አልልም ፡ ከቶ (፬x)

ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ
ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ
ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ
ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ
አያለሁ ፡ በዐይኔ (፬x)