ያኖረኛል (Yanoregnal) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ምሥጋና ፡ የተጋውን ፡ እግዚአብሔርን ፡ እጠራዋለሁኝ
መቅደሱን ፡ በዕልልታዪ ፡ እበዝማሬ ፡ እሞላዋለሁ
ይኸው ፡ ምሥጋናው ፡ ይኸው ፡ ዝማሬው
ይኸው ፡ ዕልልታው ፡ ስለሚገባው (፪x)

የሚሰዋልኝ ፡ ለእኔ ፡ ምሥጋና
እርሱ ፡ ያከብረኛል ፡ ብሎኛልና
ሞላ ፡ ጐደለ ፡ ሳልል ፡ እሰዋለሁ
በሙሉ ፡ ኃይሌ ፡ አመልከዋለሁ
አመልከዋለሁ (፬x)

ነገ ፡ ለራሱ ፡ ይጨነቅ ፡ ይጨነቅ ፡ እንጂ
እኔስ ፡ አርፌ ፡ እኖራለሁ ፡ በአምላኬ ፡ እጅ
ነገ ፡ ለራሱ ፡ ይጨነቅ ፡ ይጨነቅ ፡ እንጂ
እኔስ ፡ አርፌ ፡ እኖራለሁ ፡ በአምላኬ ፡ እጅ

አዝነገሬን ፡ በሚያውቅልኝ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ
ትላንትን ፡ ያሻገረኝ ፡ ለነገም ፡ አምነዋለሁ (፪x)
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ ገና ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል

ጠላት ፡ ዙሪያዬ ፡ ሲዞር ፡ ይውላል
አባባ ፡ ቅጥሬን ፡ በእሳት ፡ ቀጥሮታል
አያገነኝም ፡ ሌት ፡ ቀን ፡ ቢለፋ
የሚጠብቀኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አያንቀላፋም
አያንቀላፋም (፬x)

አዝነገሬን ፡ በሚያውቅልኝ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ
ትላንትን ፡ ያሻገረኝ ፡ ለነገም ፡ አምነዋለሁ (፪x)
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ ገና ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል

ሃማ ፡ በቅናት ፡ ሞትን ፡ ደግሶ
ለመርዶኪዮስ ፡ ጉድጓድ ፡ ተምሶ
መቼ ፡ ለጠላት ፡ ታልፎ ፡ ተሰጠ
አምላኩ ፡ ደርሶ ፡ ነገሩ ፡ ተገለበጠ
ተገለበጠ (፬x)

ሰምቼ ፡ ነበረ ፡ በጆሮዬ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እንደሆንክ ፡ አባብዬ
ዛሬም ፡ ዐይኔ ፡ አይታሃለች
ነፍሴ ፡ ታመሰግናለች
እንደሰማሁ ፡ እንዲሁ ፡ አየሁ (፫x) ፡ ሆ
እንደሰማሁ ፡ እንዲሁ ፡ አየሁ (፫x) ፡ ሆ

ከዘለዓለም ፡ ፍርድ ፡ ከሞት ፡ ፍርሃት
በደም ፡ ኪዳን ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ የዋጃት
በላይ ፡ በረከት ፡ አንዴ ፡ ባርኮኛል
ኢየሱስ ፡ አለልኝ ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
ምን ፡ ያሰጋኛል (፬x)

አዝ፦ ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ ገና ፡ ያሳየኛል
ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል