ትልቅ ፡ ነህ (Teleq Neh) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ዝናህን ፡ ላውራ ፡ ኦሆሆሆ ፡ ታላቅነትህን
ስላንተ ፡ ዝና ፡ አውርቼ ፡ አልጠግብም
ብናገር ፡ ብናገር (፪x)

ኦ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ኦ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ትልቅ ፡ ነህ (፬x)
ትልቅ ፡ ነህ (፬x)

ቀና ፡ ብዬ ፡ ሠማዩን ፡ ሳይ
ጨረቃዋን ፡ ከዋክብቱን ፡ ሳይ
አሻቅቤ ፡ ተራራውን ፡ ሳይ
ባሕሩን ፡ ውቅያኖሱን ፡ ሳይ
አፈጠጠሩ ፡ ይገርመኛል
አቤት ፡ ውበቱ ፡ ይደንቀኛል
ጌታዬ ፡ የአንተን ፡ ትልቅነት ፡ ያሳየኛል

አመልክሃለሁ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
አመልክሃለሁ ፡ ፊትህ ፡ ተደፍቼ
አመልክሃለሁ ፡ ክብሬን ፡ ሁሉ ፡ ትቼ
አመልክሃለሁ ፡ ወድጄ ፡ ፈቅጄ

ኦ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ እኔም ፡ አላውቅህም (፪x)
ኦ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ እኛም ፡ አናውቅህም (፪x)

የፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ ፈጣሪ
የማትመረመር ፡ መርማሪ
ጥበብህን ፡ ዕውቀትህን ፡ ማን ፡ ያውቀዋል
ፍርድህም ፡ ከማስተዋል ፡ ሁሉ ፡ ይልቃል

ኦ ፡ ለመንገድህ ፡ ፍለጋ ፡ የለው
አደራረግህ ፡ እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው
አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ትልቅ ፡ ነህ (፬x)
ትልቅ ፡ ነህ (፬x)

ውሆችን ፡ በእፍኝህ ፡ የሰፈርህ
ተራሮችን ፡ በሚዛን ፡ የመዘንህ
ሠማዩን ፡ በስንዝር ፡ የለካህ
የምድርን ፡ አፈር ፡ ሰብስበህ ፡ የያዝህ
ሁሉን ፡ ስትሰራ ፡ ማን ፡ አማክሮሃል
የፍርድን ፡ መንገድ ፡ ማን ፡ አስተምሮሃል
አቤት ፡ ጥበብህ ፡ ከሁሉ ፡ ይልቃል

ኦ ፡ አመልካህለሁ ፡ አሃ ፡ አመልክሃለሁ
አሁ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ
ኦ ፡ አመልካህለሁ ፡ አባ ፡ አመልክሃለሁ
አሁ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ