ቅዱስ ፡ ነህ (Qedus Neh) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

በረጅምና ፡ ከፍ ፡ ባለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ለተቀመጥከው (፪x)
ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ ይዤ ፡ መጣሁ ፡ ለአንተ ፡ ልሰዋ (፪x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩኝ ፡ ወደ ፡ ማደሪያህ ፡ እገባለሁኝ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩኝ ፡ ወደ ፡ መቅደስህ ፡ እገባለሁኝ

አዝቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x)
ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x)

ቅዱስ ፡ እያሉህ ፡ ሲያመልኩ ፡ መላዕክቱ
ክብርህ ፡ ቤቱን ፡ ሞልቶት ፡ ነበር ፡ ኦ ፡ አቤቱ
እኔም ፡ ከልቤ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩ ፡ እጮሃለሁ
አንተ ፡ ቅዱስ ፡ መሆንህን ፡ አውጃለሁ

አዝቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x)
አመልካሃለሁ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩኝ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ስላላየሁኝ
ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x)

ለዘለዓለም ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ተቀምጠሃል
ደፍሮ ፡ ከዙፋንህ ፡ ና ፡ ውረድ ፡ ማን ፡ ይልሃል
አይቆጠርም ፡ ዘመናትህ ፡ አንተ ፡ ጌታ
ቅዱስ ፡ እያልኩኝ ፡ ልስገድልህ ፡ በዕልልታ

አዝቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x)
ይደርደርልህ ፡ ዛሬም ፡ በገናው
በዕልልታ ፡ ሆታ ፡ ቅኔ ፡ ምሥጋናው
ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x)

ስራህ ፡ ትክክል ፡ እውነተኛ ፡ እንከን ፡ የለህ
ነውር ፡ ነቀፋ ፡ የሌለብህ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ
ፍርድ ፡ አታጓድል ፡ አታደላ ፡ ጻድቅ ፡ አምላክ
ነፍሴ ፡ ሁልጊዜ ፡ በምሥጋና ፡ አንተን ፡ ትበል

አዝቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x)

የጌታዎች ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
የአማልክት ፡ አምላክ ፡ አምላክ ፡ አምላክ ፡ የእስራኤል ፡ ቅዱስ
ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ስምህ ፡ ይወደስ
ስምህ ፡ ይቀደስ ፡ ዛሬም ፡ ልዘለዓለም

ይወደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x)
ይቀደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x)
ይወደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x)
ይቀደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x)
ይወደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x)