ቅድስና (Qedesena) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ክርስትናን ፡ መኖር ፡ መኖርን ፡ እሻለሁ
ጥማቴም ፡ ጸሎቴም ፡ አንተን ፡ ለመምሰል ፡ ነው ፡ ጌታ
ተቀድሶ ፡ መኖር ፡ መኖርን ፡ እሻለሁ ፡ አው
ጥማቴም ፡ ጸሎቴም ፡ አንተን ፡ ለመምሰል ፡ ነው ፡ አባ

እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ክብርህን ፡ ላየው ፡ ጌታ
እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ ላየው ፡ አባ

እስኪ ፡ አግዘኝ ፡ አቅም ፡ ስጠኝ
ለአንተ ፡ እንድኖር ፡ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ ፡ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ ፡ አባ ፡ አስጨክነኝ ፡ አዎ

ዓለምን ፡ በጽድቅህ ፡ ስራ ፡ እየኮነንኩኝ ፡ እህ ፡ እይኮነንኩኝ
ልኑር ፡ አንተን ፡ ኢየሱሴን ፡ እያስከበርኩኝ ፡ አዎ ፡ እያስከበርኩኝ
ቅዱሱ ፡ ስምህ ፡ በእኔ ፡ ስለተጠራ ፡ አባ ፡ ስለተጠራ
በእኔ እንዳታፍርብኝ (ስምህን እንዳላሰድብ) ፡ እርዳኝ ፡ አደራ ፡ አዎ ፡ እርዳኝ ፡ አደራ

ጉልበት ፡ ስጠኝ ፡ አቅም ፡ ስጠኝ
በጽድቅ ፡ እንድኖር ፡ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ ፡ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ ፡ አባ ፡ አስጨክነኝ ፡ አዎ

ጨለማ ፡ ለዋጣት ፡ ዓለም ፡ ብርሃን ፡ ሆኜ ፡ እህ ፡ ርሃን ፡ ሆኜ
ለትውልድ ፡ ምሳሌ ፡ አርገኝ ፡ ልኑር ፡ ጨክኜ ፡ አዎ ፡ ልኑር ፡ ጨክኜ
መራራውን ፡ አጣፋጭ ፡ የምድር ፡ ጨው ፡ አርገኝ ፡ አባ ፡ የምድር ፡ ጨው ፡ አርገኝ
ሁልጊዜ ፡ የጽድቅህ ፡ ፍሬ ፡ አይታጣብኝ ፡ አዎ ፡ አይታጣብኝ

እስኪ ፡ አግዘኝ ፡ አቅም ፡ ስጠኝ
ለአንተ ፡ እንድኖር ፡ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ ፡ አስጨክነኝ
አስጨክነኝ ፡ አባ ፡ አስጨክነኝ ፡ አዎ

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቅድስና (፬x)

ለጊዜው ፡ ለሚገኝ ፡ ደስታ ፡ ራሴን ፡ አልሸጥም ፡ አሃ ፡ ራሴምን ፡ አልሸጥም
ለኑሮ ፡ ለእንጀራ ፡ ብዬ ፡ አልሸቃቅልም ፡ አዎ ፡ አልሸቃቅልም
ይራበኝ ፡ እንጂ ፡ ልጣ ፡ ሁሉ ፡ ይቅርብኝ ፡ አዎ ፡ ሁሉ ፡ ይቅርብኝ
ጨክኜ ፡ ላገለግልህ ፡ ወስኛለሁኝ ፡ አዎ ፡ ወስኛለሁኝ

እንደልብህ ፡ ልኑርልህ
በእኔ ፡ ጌታ ፡ ደስ ፡ ይበልህ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሃ ፡ እኖራለሁ
ክብርህን ፡ ላይ ፡ ናፍቄያለሁኝ

እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ክብርህን ፡ ላየው ፡ ጌታ
እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ ላየው ፡ አባ