ማን ፡ ትሉታላችሁ (Man Telutalachehu) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ኢየሱስን ፡ ማን ፡ ትሉታላቹህ
ከማንስ ፡ ጋር ፡ ታስተያዩታላቹህ
የእኔን ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ትሉታላቹህ
ከየትኛው ፡ ታስተያዩታላቹህ

እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሞትን ፡ የረታ
ማኅተሙን ፡ ብቻውን ፡ የፈታ
የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ (፬x)

ብዙዎች ፡ ነበሩ ፡ ኃያል ፡ ነን ፡ ያሉ
ዘመን ፡ ሲቀየር ፡ እነርሱ ፡ ግን ፡ የሉ
እንዲያው ፡ በነበር ፡ ቀረ ፡ ዝናቸው
መቃብር ፡ አሉ ፡ ሞት ፡ ድል ፡ ነስቷቸው

ሞተ ፡ አበቃ ፡ አከተመለት
እያለ ፡ ሰይጣን ፡ ሲሳለቅበት
ሞት ፡ መቼ ፡ ያዘው ፡ ይህን ፡ አንበሳ
በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ
ኢየሱስ ፡ ተነሳ (፬x)

ፍጥረት ፡ ይህን ፡ ይስማ ፡ ይታወቅ ፡ እውነቱ
ሞትን ፡ ድል ፡ ያረገ ፡ እስኪ ፡ ማነው ፡ ብርቱ
መጽሃፉን ፡ ከፍቶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አሸናፊ ፡ ጌታ
አሸናፊ ፡ ጌታ (፬x)

እንደ ፡ ጋለ ፡ ነሃስ ፡ አቤት ፡ እግሮቹ
እንዴሳት ፡ ነበርላብ ፡ ናቸው ፡ ዐይኖቹ
ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ መታጠቂያ ፡ ታጥቆ
አለ ፡ ይኖራል ፡ ዘለዓለም ፡ ደምቆ

ፊቱ ፡ ከፀሐይ ፡ በላይ ፡ ያበራል
ግርማ ፡ ሞገሱ ፡ እጅግ ፡ ያስፈራል
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ የማመልከው
ሰምቶ ፡ በእሳት ፡ የሚመልሰው
የሚመልሰው (፬x)

ጌታ ፡ ነው ፡ አቻ ፡ የሌለው (፬x)
አቻ ፡ የሌለው (፬x)

በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከምድርም ፡ በታች
መቼ ፡ ተገኘ ፡ መጽሃፉን ፡ ከፋች
ዮሐንስ ፡ ሲያለቅስ ፡ ይህንን ፡ አይቶ
አታልቅስ ፡ አለው ፡ መላዕኩ ፡ መጥቶ

መጽሃፉን ፡ ሊከፍት ፡ ማኅተሙን ፡ ሊፈታ
ጀግና ፡ ተገኝቷል ፡ የጌቶች ፡ ጌታ
ከዳዊት ፡ ዘር ፡ ግንድ ፡ ያቆጠቆጠው
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሁሉን ፡ ፈታታው
ሁሉን ፡ ፈታታው (፬x)

ጌታ ፡ ነው ፡ አቻ ፡ የሌለው (፬x)
አቻ ፡ የሌለው (፬x)