ክብሬ (Kebrie) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

በምሥጋና ፡ ወደመቅደሱ ፡ እገባለሁ
ከልቤ ፡ ሆኜ ፡ እቀኛለሁ
ያከበረኝን ፡ ሰው ፡ ያረገኝን
አምላኬን ፡ አመልከዋለሁ

በምሥጋና ፡ ወደመቅደሱ ፡ እገባለሁ
ከልቤ ፡ ሆኜ ፡ እቀኛለሁ
የወደደኝን ፡ አዎ ፡ የሞተልኝን
ኢየሱሴን ፡ አከብረዋለሁ

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)

ኢየሱሴ ፡ ክብሬ ፡ ማረጌ
ኢየሱሴ ፡ የአብ ፡ ስጦታ
ኢየሱሴ ፡ ነህ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጤ
ኢየሱሴ ፡ ውበቴ ፡ ጌታ
ኢየሱሴ ፡ የምትወደድ
ኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ
ኢየሱሴ ፡ አሳዳጊዬ
ኢየሱሴ ፡ ይቧረክ ፡ ስምህ (፪x)

የሚያንኳኳ ፡ መልስ ፡ ሽቶ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ አንተን ፡ ጠርቶ
ማን ፡ አፈረ ፡ አንተን ፡ ጠርቶ (፪x)
ልመናውን ፡ ሰማህለት ፡ ሸክሙን ፡ አንተ ፡ ወሰድክለት
ሸክሙን ፡ አንተ ፡ ወሰድክለት (፪x)

ተደንቂያለሁ ፡ በማዳንህ
ተነገሮ ፡ አያልቅም ፡ ድንቅ ፡ ስራህ
መፍቻው ፡ ተገኝቶ ፡ የእንቆቅልሹ
ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኗል ፡ ዮሴፍ ፡ ትንሹ

ተዐምር ፡ ነው ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ
ከፍ ፡ በል ፡ በምሥጋናዬ
ድንቅ ፡ ነው ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ
ከፍ ፡ በል ፡ በምሥጋናዬ
ከፍ ፡ በል ፡ በምሥጋናዬ (፪x)

የቱን ፡ ትቼ ፡ የቱን ፡ ላውራ
ኢየሱሴ ፡ የአንተን ፡ ስራ (፪x)
ባይመጥንም ፡ ምሥጋናዬ
ይኸውልህ ፡ አባብዬ (፪x)

ሰው ፡ የናቀውን ፡ የገፋውን ፡ መቼ ፡ ተውከው ፡ ብቸኛውን
መቼ ፡ ተውከው ፡ ብቸኛውን (፪x)
አከበርከው ፡ በአደባባይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጣለት ፡ ከሠማይ
ትዕዛዝ ፡ ወጣለት ፡ ከሠማይ (፪x)

አይቻለሁኝ ፡ ስትረዳ
ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ለተጐዳ
እጄን ፡ በእጆችህ ፡ ይዘህ ፡ መራህ
ያልገመትኩትኝ ፡ ክብር ፡ አሳየኸኝ

ማረጌ ፡ ክብሬ ፡ ኢየሱሴ
ላምልክህ ፡ ከልብ ፡ ከነፍሴ
ማረጌ ፡ ክብሬ ፡ ኢየሱሴ
ላድንቅህ ፡ ከልብ ፡ ከነፍሴ
ላምልክህ ፡ ከልቤ ፡ ኢየሱሴ
ላምልክህ ፡ ከልብ ፡ ከነፍሴ

ኢየሱሴ ፡ የመዳን ፡ ቀንዴ
ኢየሱሴ ፡ መታመኛዬ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ውዴ
ኢየሱሴ ፡ ወንድም ፡ ጋሻዬ
ኢየሱሴ ፡ ምትክም ፡ የለህ
ኢየሱሴ ፡ የፍቅር ፡ ምርጫዬ