ሃገሬ (Hagerie) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

"እሄዳለሁ ፡ ሃገሬ ፡ ጌታዬን ፡ አየዋለሁኝ
ላየው ፡ ፊትለፊቱ"

ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማያት
በጉ ፡ ብርሃኗ ፡ የሆነላት ፡ የሆነላት
ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማያት
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ያዘጋጃት (፫x)

እንግዳ ፡ ነኝና ፡ አልሆንም ፡ ቤተኛ (፪x)
ሃገሬ ፡ ሠማይ ፡ ነው ፡ በላይ ፡ ርስት ፡ አለኛ ፡ በላይ ፡ ቤት ፡ አለኛ
ተዘጋጅቼ ፡ ልጠብቀው ፡ ቤቴን ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ ላሰናዳው
ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል ፤ ይመጣል ፡ እርሱ ፡ ይመጣል (፪x)

አሃሃሃ ፡ አልዘናጋም ፡ አሃሃሃ ፡ ጠፊውን ፡ አይቼ
አሃሃሃ ፡ በላዬ ፡ ላከማች ፡ አሃሃሃ ፡ ልስራ ፡ ተግቼ
አሃሃሃ ፡ እርሱ ፡ ይመጣል ፡ አሃሃሃ ፡ ወይ ፡ እሄዳለሁ
አሃሃሃ ፡ እንደስራዬ ፡ አሃሃሃ ፡ እቀበላለሁ

ዐይን ፡ ያላያት ፡ የሰው ፡ እጅ ፡ ያልሰራት
ለልጆቹ ፡ ጌታ ፡ ያዘጋጃት
ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማይ (፪x)
የቅዱሳን ፡ የጻድቃን ፡ ከተማ
ቀኑ ፡ ቀርቧል ፡ ወደዚያ ፡ ልገባ
ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማይ (፪x)

መታረት ፡ መራቆት ፡ መራብም ፡ ያልፍና
ሰቆቃው ፡ ሃዘኑ ፡ ሁሉ ፡ ይረሳና
ጌታዬን ፡ ፊትለፊት ፡ በክብር ፡ አያለሁ
ናፍቆቴን ፡ ደስታዬን ፡ ያኔ ፡ እወጣለሁ

ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል
ይመጣል ፡ እርሱ ፡ ይመጣል (፪x)

የፍጻሜው ፡ መለከት ፡ ይነፋል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በክብር ፡ ይመጣል
ሃገር ፡ አለን ፡ እኛስ ፡ በሠማይ (፪x)
በቅጽበት ፡ ዐይን ፡ ሁሉ ፡ ይለወጥና
እንሄዳለን ፡ ልንኖር ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
ሃገር ፡ አለን ፡ እኛስ ፡ በሠማይ (፪x)

የዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ አላፊ ፡ ጠፊ ፡ ነው
ውበት ፡ ደም ፡ ግባትም ፡ ሁሉ ፡ ረጋፊ ፡ ነው
ጌታዬ ፡ ሲመጣ ፡ እንዳየው ፡ ሳላፍር
ሥጋዪን ፡ ልጐስም ፡ ልኑር ፡ ለእርሱ ፡ ክብር

ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል
ይመጣል ፡ እርሱ ፡ ይመጣል (፪x)

እዚህ ፡ ነዋሪ ፡ አይደለሁም ፡ አይደለሁም
እንግዳ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ቆይታዬ ፡ ያበቃና ፡ ይፈጸማል ፡ እሄዳለሁ ፡ ሃገሬ
ሃገሬ ፡ በሠማይ ፡ ሃገሬ
ሃገሬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ሃገሬ
ሃገሬ ፡ በሠማይ ፡ ሃገሬ
ሃገሬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ሃገሬ (፪x)