ፍቅር (Feqer) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

እንደበግ ፡ ሲነዳ ፡ አሁን ፡ አልከፈተም
ወስደው ፡ ሲያንገላቱት ፡ አንዳች ፡ አልመለሰም (፪x)
አስጨነቁት ፡ በጅራፍ ፡ ገረፉት
በአደባባይ ፡ እርቃኑን ፡ ሰቀሉት
ቤዛ ፡ ሆነ ፡ በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ስለእኔ ፡ ተመታ

ፍቅር ፡ ጐልጐታ ፡ ላይ
ፍቅር ፡ ቀራኒዮ ፡ ላይ (፪x)
እዩት ፡ እየሲሴን ፡ እዩት ፡ ስቃዩ ፡ ሲያይል
እዩት ፡ አባብዬን ፡ እዩት ፡ ሲቃዩ ፡ ሲያይል
ስቃዩ ፡ ሲያይል (፬x)

ለእኔ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ መንከራተቱ
ለእኔ ፡ ነው ፡ ስቃይን ፡ ማየቱ
ለእኔ ፡ ነው ፡ ሲዘባበቱበት
ለእኔ ፡ ነው ፡ የበዛው ፡ ትዕግሥቱ
ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ያለው
ለእኔ ፡ ነዋ ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ያላበው
ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ህመሜ ፡ ያመመው
ለእኔ ፡ ነዋ ፡ በጦር ፡ የተወጋው
ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነዋ (፬x)

አባት ፡ ሆይ ፡ ፈቃድህ ፡ ያልከው ፡ ይሁን ፡ ብሎ
መራራውን ፡ ጽዋ ፡ ጠጣው ፡ ተንጠልጥሎ (፪x)
አፈረሰው ፡ የጥሉን ፡ ግድግዳ ፡ አስታረቀን ፡ እኛን ፡ ከአብ ፡ ጋራ
ኢየሱሴ ፡ ጣልቃ ፡ ገብቶ ፡ አንድ ፡ አደረገን ፡ ሞቶ

ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ
ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ብሎ ፡ የዋተተው
ለእኔ ፡ ነዋ ፡ ጀርባውን ፡ በጅራፍ
ለእኔ ፡ ነዋ ፡ የተተለተለው
ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነዋ (፬x)

የድካሙን ፡ ዋጋ ፡ ፍሬውን ፡ ሊያይ
ታገሰ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ሲቀበል ፡ ስቃይ (፪x)
የተናቀ ፡ ደግሞም ፡ የተጠላ
የህማም ፡ ሰው ፡ መሰለ ፡ ተላላ
በቁስሎቹ ፡ ተፈውሻለሁ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ

ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ ነዋ (፬x)